20 ሞትና መቃብር በቃን እንደማይሉ፥ የሰው ምኞትም እንደዚሁ ነው።
20 ሲኦልና የሙታን ዓለም እንደማይጠግቡ ሁሉ፣ የሰውም ዐይን አይረካም።
20 ሲኦልና ጥፋት እንደማይጠግቡ፥ እንዲሁ የሰው ዐይን አይጠግብም።
የሙታን ዓለም በእግዚአብሔር ፊት ግልጥልጥ ያለ ነው፤ ምንም ነገር ሊሸፍነው አይችልም።
እግዚአብሔር በሲኦልና በጥፋት ቦታ ያለውን የሚያይ ከሆነ በልባችን ውስጥ ያለውንማ እንዴት አያይም?
እንዲህ ዐይነቱ ሀብት እያየኸው ወዲያው ይጠፋል፤ በሰማይ እንደ ሚበርር ንስር ክንፍ አውጥቶ ይበራል።
ውሃ እንደ መስተዋት ሆኖ ፊትህን እንደሚያሳይህ ኅሊናህም እንደ መስተዋት ሆኖ የራስህን ጠባይ መልሶ ያሳይሃል።
ሁሉ ነገር አሰልቺ ነው፤ አሰልቺነቱንም ሰው በቃል ገልጦ ሊናገረው እንኳ አይችልም፤ ዐይን አይቶ አይጠግብም፤ ጆሮም ሰምቶ በቃኝ አይልም።
እነሆ፥ ብቻውን የሚኖር አንድ ሰው አለ፤ ልጅም ሆነ ወንድም የለውም፤ ይሁን እንጂ ዘወትር በሥራ ከመድከም አይቦዝንም፤ ባገኘውም ሀብት በቃኝ ማለትን አላወቀም፤ “እርሱም የምደክመው ለማን ነው? ለራሴስ ደስታን የምነፍገው ለምንድን ነው?” ብሎ ራሱን ይጠይቃል፤ ይህ ሁሉ የባሰ ከንቱና የሥቃይ ሕይወት ነው።
ሰው በሥራ መድከሙ የሚበላውን ነገር ለማግኘት ነበር፤ ይሁን እንጂ “በቃኝ!” ማለት አያውቅም።
መቃብር ሆድዋን አስፍታ፥ አፍዋን ከፍታ ትጠብቃቸዋለች፤ የኢየሩሳሌምን መሳፍንትና ተሰብስቦ የሚያወካ ሕዝብዋን ትውጣለች።
የአንተ ሥራ ንጹሕ ደምን ማፍሰስና ሰውን መጨቈን ነው፤ ዐይንህና ልብህም የሚያተኲሩት አጭበርብሮ ትርፍን በማግበስበስ ላይ ብቻ ነው።
በእርግጥ ሀብት ሰውን ያታልላል፤ ትምክሕተኛ ሰው ዕረፍት የለውም፤ እንደ መቃብር ስስታም እንደ ሞትም በቃኝ የማይል ስለ ሆነ መንግሥታትን ሁሉ ለራሱ ይወራል፤ ሕዝቦችንም ይማርካል።
“እናንተማ ብዙ መከር ለመሰብሰብ ዐቅዳችሁ ነበር፤ ነገር ግን ጥቂት ሆነ፤ ያንኑንም ወደ ቤት ባስገባችሁ ጊዜ እኔ እፍ ስላልኩበት ጠፋ፤ ይህንንስ ያደረግኹት ለምን ይመስላችኋል? እኔ ይህን ያደረግኹት፥ ከእናንተ እያንዳንዱ ቤቱን አስጊጦ እየሠራ የእኔ ቤተ መቅደስ ፍርስራሽ ሆኖ በመቅረቱ ነው።
በዓለም ያለው ሁሉ የሥጋ ምኞት፥ የዐይን አምሮት፥ የኑሮ ትምክሕት ከዓለም ነው እንጂ ከእግዚአብሔር አብ አይደለም።