Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 13:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሀብታም በገንዘብ ሕይወቱን ለማዳን ይጣጣራል፤ ድኻ ግን የሚወሰድበት ሀብት ስለሌለው አይጨነቅም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የሰው ሀብቱ ለሕይወቱ ቤዛ ሊሆነው ይችላል፤ ድኻው ግን ሥጋት የለበትም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፥ ድሀ ግን ተግሣጽን አይሰማም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፤ ድሃ ግን ቍጣን አይቃወምም።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 13:8
15 Referencias Cruzadas  

ናቡከደነፆር የኢየሩሳሌምን ሕዝብ፥ ልዑላን መሳፍንቱን ሁሉና ሌሎችንም ታላላቅ ሰዎችን ጭምር በድምሩ ዐሥር ሺህ ሰዎች ማርኮ ወሰደ፤ ከእነርሱም ጋር የእጅ ጥበብ ዐዋቂዎችንና የብረት አንጣሪዎችን ሁሉ ወሰደ፤ በይሁዳ እንዲቀሩ ያደረገው የመጨረሻዎችን ድኾች ብቻ ነበር።


ነገር ግን ምንም ሀብት የሌላቸውን የመጨረሻ ድኾች፥ አትክልት ኰትኳቾችና መሬት አራሾች ይሆኑ ዘንድ በይሁዳ ምድር ትቶአቸው ሄደ።


ሰይጣንም “በቊርበት ፈንታ ቊርበት” እንዲሉ፥ “ሰው እኮ ሕይወቱን ለማትረፍ ሲል ያለውን ሁሉ ይሰጣል።


ሆኖም ባለ ንብረቱ ሕይወቱን ለመዋጀት ካሣ እንዲከፍል ከተፈቀደለት ካሣውን በሙሉ ይክፈል።


አንዳንድ ሰዎች ምንም ሳይኖራቸው ሀብታም መስለው ለመታየት ይጥራሉ፤ ሌሎች ደግሞ ብዙ ሀብት እያላቸው፥ ምንም ሀብት እንደሌላቸው መስለው ይኖራሉ።


የጻድቃን ብርሃን ያንጸባርቃል፤ የኃጢአተኞች መብራት ግን ይጠፋል።


የብልኆች ዘውድ ጥበባቸው ነው፤ የሞኞች ጌጥ ግን ሞኝነታቸው ነው።


ምንም ዐይነት ካሳ መቀበል አይፈልግም፤ የስጦታም ብዛት ቊጣውን አያበርድለትም።


ምንም ሀብት ያልነበራቸውን ድኾች ብቻ በይሁዳ ምድር ተወ፤ ለእነርሱም የወይን ተክል ቦታዎችንና የሚያርሱት መሬት ሰጣቸው።


ከእነዚያ ሰማኒያ ሰዎች መካከል በተለይ ዐሥሩ ሰዎች “እባክህ አትግደለን! እኛ በእርሻ ውስጥ የደበቅነው ብዙ ስንዴ፥ ገብስ፥ የወይራ ዘይትና ማር. አለን” ብለው እስማኤልን ለመኑት። እርሱም ምሕረት አደረገላቸው።


ከመካከላችሁ ራሳቸውን ዝቅ ያደረጉ ትሑታን ሰዎችን አስቀራለሁ፤ እነርሱም በእኔ የሚታመኑና የእኔንም ርዳታ የሚሹ ይሆናሉ።


ሰው የዓለሙን ሁሉ ሀብት ቢያገኝ፥ ነፍሱን ግን ቢያጠፋ፥ ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ዋጋ ሊከፍል ይችላል?


ከምግብ ሕይወት፥ ከልብስም ሰውነት ይበልጣል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos