Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 5:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 “ከዚህ በኋላ ካህኑ ይህን የእርግማን ቃል ይጽፈዋል፤ ጽሕፈቱንም አጥቦ የመራራ ውሃ ባለበት ዕቃ ውስጥ ይጨምረዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 “ ‘ካህኑ እነዚህን መርገሞች በሰሌዳ ላይ ይጻፍ፤ በመራራውም ውሃ ይደምስሳቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 “ካህኑም እነዚህን መርገሞች በሰሌዳ ላይ ይጽፋቸዋል፥ በመራራውም ውኃ ያጠፋቸዋል፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 “ካህ​ኑም እነ​ዚ​ህን መር​ገ​ሞች በሰ​ሌዳ ላይ ይጽ​ፋ​ቸ​ዋል፤ በመ​ር​ገ​ሙም መራራ ውኃ ይደ​መ​ስ​ሳ​ቸ​ዋል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ካህኑም እነዚህን መርገሞች በሰሌዳ ይጽፈዋል፥ በመራራውም ውኃ ይደመስሰዋል፤

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 5:23
14 Referencias Cruzadas  

ታናናሾችንና ታላላቆችን ሙታን በዙፋኑ ፊት ቆመው አየሁ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ፤ የሕይወት መጽሐፍ የሆነ ሌላ መጽሐፍም ተከፈተ፤ ሙታንም በመጻሕፍቱ ተጽፎ በተገኘው ሥራቸው መሠረት ፍርድ ተቀበሉ፤


እንግዲህ ኃጢአታችሁ እንዲደመሰስላችሁ ንስሓ ገብታችሁ ወደ ጌታ ተመለሱ፤


በደልህን እንደ ደመና ኃጢአትህን እንደ ማለዳ ጭጋግ አስወግጄአለሁ፤ ስለ አዳንኩህ ወደ እኔ ተመለስ።”


ይህም ሁሉ ሆኖ ኃጢአታችሁን ይቅር የምል አምላክ እኔ ነኝ፤ ይህንንም የማደርገው ስለ እናንተ ሳይሆን ስለ እኔነቴ ነው፤ ስለዚህ ኃጢአታችሁን አልቈጥርባችሁም።


ፊትህን ከኃጢአቴ መልስ፤ በደሌን ሁሉ ደምስስ።


አምላክ ሆይ! ስለ ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ይቅር በለኝ፤ ስለ ታላቁ ምሕረትህም ኃጢአቴን ደምስስልኝ።


“ምነው የሚሰማኝ ባገኘሁ! መከላከያዬን አቀርባለሁ፤ ሁሉን ቻይ አምላክ ይመልስልኝ! ምነው ከሳሼም የክሱን ዝርዝር በጽሑፍ አቅርቦልኝ ባየሁት!


ቃሉም እንዲህ የሚል ነበር፦ “እኔ እግዚአብሔር ለይሁዳ ንጉሥ በተነበበለት መጽሐፍ ውስጥ በሚገኙት እርግማኖች ኢየሩሳሌምንና ሕዝብዋን ሁሉ እቀጣለሁ፤


“ይህን መዝሙር ጽፈህ ለእስራኤላውያን አስተምራቸውና እንዲዘምሩት አድርግ፤ ይህም መዝሙር በእነርሱ ላይ ማስረጃ ይሆንልኛል።


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን “ዘወትር ሲታወስ እንዲኖር የዚህን ድል ታሪክ ጻፈው፤ ለኢያሱም ዐማሌቃውያንን ከምድር ጨርሼ የማጠፋቸው መሆኔን ንገረው” አለው።


ይህም ውሃ ወደ ሰውነትሽ ገብቶ ሆድሽን ያሳብጠው፤ ማሕፀንሽንም ያኰማትረው።’ ሴትዮዋም ‘አሜን፥ እግዚአብሔር እንዲሁ ያድርግብኝ’ ብላ ትመልሳለች።


ሴትዮዋ ብርቱ ሕመም የሚያስከትልባትን መራራ ውሃ እንድትጠጣ ከማድረጉ በፊት፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios