Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 4:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “ለእግዚአብሔር የሚቀርበው የተቀደሰ ኅብስት ማኖሪያ የሆነውንም ገበታ በሰማያዊ ጨርቅ ይሸፍኑት፤ በገበታውም ላይ ሳሕኖችን፥ ጭልፋዎችን፥ ጽዋዎችንና የወይን ጠጅ መቅጃዎችን ያኑሩ፤ ኅብስትም ዘወትር በእርሱ ላይ ይኑርበት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “በገጸ ኅብስቱ ገበታ ላይ ሰማያዊ ጨርቅ ይዘርጉበት፤ በላዩም ላይ ወጭቶች፣ ጭልፋዎች፣ ጽዋዎች፣ ለመጠጥ ቍርባን የሚሆኑትን ማንቈርቈሪያዎች እንዲሁም ሁልጊዜ ከዚያ የማይታጣውን ኅብስት ያስቀምጡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በተቀደሰው ኅብስቱ ገበታ ላይ ሰማያዊውን መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤ በእርሱም ላይ ወጭቶቹን፥ ሙዳዮችንም፥ ጽዋዎቹንም፥ ለመጠጥ ቁርባንም መንቀሎቹን ያስቀምጡበት፤ ሁልጊዜም የሚቀርበው እንጀራ በእርሱ ላይ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በኅ​ብ​ስተ ገጹ ገበታ ላይም ሰማ​ያ​ዊ​ውን መጐ​ና​ጸ​ፊያ ይዘ​ር​ጉ​በት፤ በእ​ር​ሱም ላይ ወጭ​ቶ​ቹን፥ ጭል​ፋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ጽዋ​ዎ​ቹ​ንም፥ ለማ​ፍ​ሰ​ስም መቅ​ጃ​ዎ​ቹን ያድ​ር​ጉ​በት፤ ሁል​ጊ​ዜም የሚ​ኖር ኅብ​ስት በእ​ርሱ ላይ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በገጽ ኅብስት ገበታ ላይ ሰማያዊውን መጐናጸፊያ ይዘርጉበት፤ በእርሱም ላይ ወጭቶቹን፥ ጭልፋዎቹንም፥ ጽዋዎቹንም፥ ለማፍሰስም መቅጃዎቹን ያድርጉ፤ ሁልጊዜም የሚኖር እንጀራ በእርሱ ላይ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 4:7
5 Referencias Cruzadas  

እርሱ ወደ እግዚአብሔር ቤት ገብቶ ከካህናት በስተቀር እርሱም ሆነ አብረውት የነበሩት ሰዎች ሊበሉት ያልተፈቀደውን፥ የተቀደሰ ኅብስት በላ።


ይህን ሁሉ በቀይ ጨርቅ ሸፍነው ከበላዩ የተለፋ ስስ ቊርበት ይደርቡ፤ መሎጊያዎችንም ያስገቡ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios