Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 35:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 የሟች ዘመድ አግኝቶ ከገደለው የዚህ ዐይነቱ የበቀል እርምጃ በነፍሰ ገዳይነት አያስጠይቅም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ደም ተበቃዩም ከከተማው ውጭ ካገኘው፣ ተከሳሹን ሊገድለው ይችላል፤ በነፍሰ ገዳይነትም አይጠየቅም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ደም ተበቃዩም ከመማፀኛው ከተማ ድንበር ውጭ ቢያገኘው፥ ደም ተበቃዩም ነፍሰ ገዳዩን ቢገድለው፥ የደም ዕዳ አይሆንበትም፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ባለ ደሙም ነፍሰ ገዳ​ዩን ቢገ​ድ​ለው፥ በደል የለ​በ​ትም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ደም ተበቃዩም ከመማፀኛው ከተማ ዳርቻ ውጭ ቢያገኘው፥ ደም ተበቃዩም ነፍሰ ገዳዩን ቢገድለው፥ የደም ዕዳ አይሆንበትም፤

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 35:27
5 Referencias Cruzadas  

ሌባው የሰረቀውን ይመልስ፤ የሚከፍለው ቢያጣ በባሪያነት ይሸጥ፤ የሰረቀው እንስሳ ላምም ቢሆን፥ አህያም ቢሆን፥ ወይም በግ ቢሆንና በሕይወት በእጁ ቢገኝ ለያንዳንዱ እንስሳ እጥፍ ዋጋ ይክፈል። “አንድ ሌባ ቤት ሰብሮ ሲገባ ቢያዝና ተመትቶ ቢገደል ተከላካዩ ለደሙ ተጠያቂ አይሆንም። ሌባው ሰብሮ የገባው ፀሐይ ከወጣ በኋላ ሆኖ ተመትቶ ቢገደል ግን ተከላካዩ ለደሙ ተጠያቂ ይሆናል።


በግድያ ወንጀል የተከሰሰው ሰው አምልጦ ከመማጸኛው ከተማ ለቆ ከሄደ፥


በግድያ ወንጀል የተከሰሰው ሰው ሊቀ ካህናቱ እስኪሞት ድረስ በዚያው በመማጸኛ ከተማ መቈየት አለበት፤ ሊቀ ካህናቱ ከሞተ በኋላ ግን ወደ ቤቱ መመለስ ይችላል፤


ይህንንም የምታደርገው እግዚአብሔር አምላክህ እንድትኖርባት ርስት አድርጎ በሚሰጥህ ምድር ንጹሕ ደም እንዳይፈስስና አንተም የደሙ ተጠያቂ እንዳትሆን ነው።


ያለው የመጠለያ ከተማ፥ ርቀቱ ቶሎ የማይደረስበት ቢሆን ግን፥ ደሙን ለመበቀል መብት ያለው የሟቹ ዘመድ አባሮ ይዞ በደል የሌለበትን ያን ሰው በቊጣ ሊገድለው ይችላል፤ በእርግጥም ያ ሰው ጠላቱ ያልሆነውን ሰው የገደለው በአጋጣሚ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos