Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 29:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከመደበኛው የሚቃጠል መሥዋዕት፥ የእህል ቊርባንና የመጠጥ ቊርባን ሌላ በተጨማሪ ለኃጢአት ማስተስረያ መሥዋዕት የሚሆን አንድ ተባዕት ፍየል አቅርቡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ደግሞም ከእህሉ ቍርባንና ከመጠጡ ቍርባን ጋራ በመደበኛነት ከሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት ሌላ አንድ ተባዕት ፍየል የኀጢአት መሥዋዕት አድርጋችሁ በተጨማሪ አቅርቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ዘወትርም ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቁርባን ከመጠጡም ቁርባን ሌላ ለኃጢአት መሥዋዕት ደግሞ አንድ አውራ ፍየል አቅርቡ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል፥ በዘ​ወ​ትር ከሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕ​ትና ከእ​ህሉ ቍር​ባን፥ ከመ​ጠ​ጡም ቍር​ባን ሌላ ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ለኃጢአትም መሥዋዕት አንድ አውራ ፍየል፥ በዘወትር ከሚቃጠለው መሥዋዕትና ከእህሉ ቍርባን ከመጠጡም ቍርባን ሌላ ታቀርባላችሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 29:22
6 Referencias Cruzadas  

ሌሎች አማልክትን የሚያመልኩ ብዙ ሐዘን ይደርስባቸዋል፤ እኔ እንደነዚህ ላሉት አማልክት የደም መሥዋዕትን አላቀርብም፤ እነርሱንም አላመልክም።


ለአምላካችሁ የምታቀርቡት የእህልም ሆነ የወይን ጠጅ መባ ስለሌለ እናንተ የአምላኬ አገልጋዮች የሆናችሁ ካህናት! ኑና ማቅ ለብሳችሁ ሌሊቱን ሁሉ አልቅሱ! እናንተም በመሠዊያው ላይ የምታገለግሉ ዋይ! ዋይ! በሉ።


በእግዚአብሔር ቤት መባ ሆኖ የሚቀርብ እህልም ሆነ የወይን ጠጅ በመታጣቱ፥ የእግዚአብሔር አገልጋዮች የሆኑት ካህናት ያለቅሳሉ።


ምናልባት እግዚአብሔር አምላካችሁ ቊጣውን መልሶ፥ በረከቱን ይሰጣችሁ ይሆናል፤ እናንተም በዚያን ጊዜ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር የእህልና የመጠጥ ቊርባን ታቀርባላችሁ።


የእህሉን ቊርባንና የመጠጡን ቊርባን ከኰርማዎቹ ከአውራ በጎቹ፥ ከጠቦቶቹ መሥዋዕት ጋር እንደየብዛታቸው በተወሰነው መሠረት ታቀርባላችሁ።


“በአራተኛው ቀን ነውር የሌለባቸው ዐሥር ኰርማዎች፥ ሁለት አውራ በጎች፥ አንድ ዓመት የሞላቸው ዐሥራ አራት ተባዕት የበግ ጠቦቶች ታቀርባላችሁ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos