Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘኍል 16:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

39 ስለዚህ አልዓዛር ጥናዎቹን ወስዶ ለመሠዊያው ክዳን ይሆኑ ዘንድ በስሱ ቀጠቀጣቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

39 ከዚህ የተነሣም ካህኑ አልዓዛር የተቃጠሉት ሰዎች አምጥተዋቸው የነበሩትን የናስ ጥናዎች ሰብስቦ የመሠዊያው መለበጫ እንዲሆኑ ቀጠቀጣቸው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

39 ካህኑም አልዓዛር የተቃጠሉት ሰዎች ያቀረቡአቸውን የናስ ጥናዎች ወሰደ፤ እነርሱንም ጠፈጠፏቸው ለመሠዊያው መለበጫ አደረጓቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

39 የካ​ህ​ኑም የአ​ሮን ልጅ አል​ዓ​ዛር የተ​ቃ​ጠ​ሉት ሰዎች ያቀ​ረ​ቡ​አ​ቸ​ውን የናስ ጥና​ዎች ወስዶ ጠፍ​ጥ​ፎም ለመ​ሠ​ዊያ መለ​በጫ አደ​ረ​ጋ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

39 ካህኑም አልዓዛር የተቃጠሉት ሰዎች ያቀረቡአቸውን የናስ ጥናዎች ወስዶ ጠፍጥፎም ለመሠዊያው መለበጫ አደረጋቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 16:39
5 Referencias Cruzadas  

ጥናዎቹም የተቀደሱት ወደ እግዚአብሔር መሠዊያ በቀረቡ ጊዜ ነው፤ ስለዚህ በኃጢአታቸው የተገደሉትን የእነዚህን ሰዎች ጥናዎች ውሰድና በመቀጥቀጥ እንዲሳሱ አድርግ፤ ለመሠዊያውም መክደኛ እንዲሆኑ አድርገህ ሥራቸው፤ ለእስራኤል ሕዝብ የመቀጣጫ ማስጠንቀቂያ ይሆናል።”


ይህም ሁኔታ የአሮን ዘር ያልሆነ ማንኛውም ሰው ለእግዚአብሔር ዕጣን ያጥን ዘንድ ወደ መሠዊያው መቅረብ እንደማይገባው ለእስራኤላውያን ሁሉ ማስጠንቀቂያ ይሆናል፤ ይህ ካልሆነ ግን እንዲህ የሚያደርግ ሰው ሁሉ እንደ ቆሬና እንደ ተከታዮቹ ይጠፋል፤ ይህም ሁሉ የተፈጸመው እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ነበር።


እንዲህም አሉት፦ “ዖዝያ ሆይ! አንተ ለእግዚአብሔር ዕጣን ታጥን ዘንድ አይገባህም፤ ይህን ለማድረግ የተመደቡት ለእግዚአብሔር የተለዩት የአሮን ልጆች የሆኑት ካህናት ብቻ ናቸው፤ ስለዚህ ከዚህ ከተቀደሰው ስፍራ ውጣ፥ እግዚአብሔር አምላክን አሳዝነሃል፤ ይህም ከእግዚአብሔር ዘንድ ክብርን የሚያስገኝልህ ድርጊት አይደለም።”


ናዳብና አቢሁ ምንም ዘር ሳይተኩ አባታቸው ከመሞቱ በፊት ሞቱ፤ ስለዚህ የእነርሱ ወንድሞች አልዓዛርና ኢታማር ካህናት ሆኑ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios