Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ነህምያ 3:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 የሔናዳድ ልጅ ቢኑይ ከዐዛርያ ቤት አንሥቶ እስከ ቅጽሩ ማእዘን ያለውን ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ከርሱም ቀጥሎ ከዓዛርያስ ቤት ጀምሮ እስከ ማእዘኑና እስከ ማእዘኑም ጫፍ ያለውን ሌላውን ክፍል የኤንሐዳድ ልጅ ቢንዊ መልሶ ሠራ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ከእርሱም በኋላ የሔናዳድ ልጅ ቢኑይ ከዓዛርያ ቤት ጀምሮ እስከ የግንቡ መደገፊያ ድረስ ሌላውን ክፍል አደሰ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ከእ​ር​ሱም በኋላ የኢ​ን​ሓ​ዳድ ልጅ ባኒ ከዓ​ዛ​ር​ያስ ቤት ጀምሮ እስከ ማዕ​ዘኑ እስከ ግን​ቡ​መ​ዞ​ሪያ ድረስ ያለ​ውን ሌላ​ውን ክፍል ሠራ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ከእርሱም በኋላ የኤንሐደድ ልጅ ቢንዊ ከዓዛርያስ ቤት ጀምሮ እስከ ማዕዘኑ ድረስ ሌላውን ክፍል አደሰ።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 3:24
7 Referencias Cruzadas  

የምጽጳ ወረዳ ገዥ የሆነው የኢያሱ ልጅ ዔዜር በጦር መሣሪያው ግምጃ ቤት ፊት ለፊት ያለውን እስከ ቅጽሩ መመለሻ ማእዘን ድረስ ያለውን ሁሉ ሠራ።


ከሌዋውያን ወገን፦ የአዛንያ ልጅ ኢያሱ፥ የሔናዳድ ጐሣ የሆነው ቢኑይ፥ ቃድሚኤል፥ ሸባንያ፥ ሆዲያ፥ ቀሊጣ፥ ፐላያ፥ ሐናን፥ ሚካ፥ ረሖብ፥ ሐሻብያ፥ ዛኩር፥ ሼሬብያ፥ ሸባንያ፥ ሆዲያ፥ ባኒና በኒኑ።


የተቆዓ ሰዎችም ከዚያ ቀጥለው ለሁለተኛ ጊዜ ለቤተ መቅደሱ መጠበቂያ ከተሠራው ከታላቁ ግንብ ፊት ለፊት ጀምሮ በዖፌል አጠገብ እስከሚገኘው ቅጽር ያለውን ሠሩ።


የሓሪም ልጅ ማልኪያና የፓሐትሞአብ ልጅ ሐሹብ ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍልና “የእቶን ግንብ” ተብሎ የሚጠራውን ግንብ ሠሩ።


ከእነርሱም ቀጥሎ ብንያምና ሐሹብ በመኖሪያ ቤቶቻቸው ፊት ለፊት ያለውን ክፍል ሠሩ። የዐናኒያ የልጅ ልጅ የሆነውም የመዕሤያ ልጅ ዐዛርያ በራሱ መኖሪያ ቤት አጠገብ ያለውን ክፍል ሠራ።


ሌዋዊው ኢያሱና ወንዶች ልጆቹ፥ እንዲሁም ዘመዶቹ፥ ቃድሚኤልና ከሖዳዊያ ቤተሰብ ወገን የሆኑ ወንዶች ልጆቹም ሁሉ በአንድነት ተባብረው ቤተ መቅደሱን እንደገና የመሥራቱን ኀላፊነት ተረከቡ፤ የሔናዳድ ዘሮች የሆኑት ሌዋውያንም ይረዱአቸው ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios