Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ነህምያ 2:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ንጉሠ ነገሥቱን፦ “ንጉሥ ሆይ፥ በአንተ ፊት ሞገስን አግኝቼ ከሆነና ጥያቄዬን ከተቀበልከኝ፥ የቀድሞ አባቶቼ ወደተቀበሩባት በይሁዳ ወደምትገኘው ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ እንድሄድና ከተማይቱን እንደገና መሥራት እንድችል ፍቀድልኝ” ብዬ ለመንኩት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ለንጉሡም፣ “ንጉሡን ደስ የሚያሠኘው ቢሆንና ባሪያህ በፊትህ ሞገስ ቢያገኝ፣ እንደ ገና እንድሠራት አባቶቼ ወደ ተቀበሩባት ወደ ይሁዳ ከተማ እንድሄድ ይፈቀድልኝ” አልሁት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ንጉሡንም፦ “ንጉሡን ደስ ቢያሰኘው፥ አገልጋይህም በፊትህ ሞገስ ቢያገኝ፥ መልሼ እንድሠራው የአባቶቼ መቃብር ወዳለበት ከተማ ወደ ይሁዳ እንድትልከኝ ነው” አልሁት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ንጉ​ሡ​ንም፥ “ንጉ​ሡን ደስ ቢያ​ሰ​ኝህ፥ ባሪ​ያ​ህም በፊ​ትህ ሞገስ ቢያ​ገኝ፥ እሠ​ራው ዘንድ ወደ ይሁዳ ወደ አባ​ቶች መቃ​ብር ከተማ ስደ​ደኝ” አል​ሁት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ንጉሡንም፦ “ንጉሡን ደስ ቢያሰኝህ፥ ባሪያህም በፊትህ ሞገስ ቢያገኝ፥ እሠራው ዘንድ ወደ ይሁዳ ወደ አባቶቼ መቃብር ከተማ ስደደኝ” አልሁት።

Ver Capítulo Copiar




ነህምያ 2:5
12 Referencias Cruzadas  

ኢዮአብም በዳዊት ፊት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ በመንሣት በአክብሮት ንጉሡን አመሰገነ፤ “የፈለግኹትን እንዳደርግ በመፍቀድህ በፊትህ ሞገስ ማግኘቴን አሁን ተረዳሁ” አለ።


“ንጉሥ ሆይ! እንግዲህ በእርግጥ ይህ ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም ይሠራ ዘንድ ንጉሥ ቂሮስ የሰጠው ትእዛዝ መኖር አለመኖሩን ለማረጋገጥ በባቢሎን ቤተ መንግሥት የጽሑፍ ማስረጃዎችን አስመርምረህ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ዐይነት ውሳኔ ቢሰጥ እንደምትፈቅድ ታስታውቀን ዘንድ እንለምናለን።”


ንጉሠ ነገሥቱም “ታዲያ፥ አሁን የምትፈልገው ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀኝ፤ እኔም ወደ ሰማይ አምላክ ከጸለይሁ በኋላ፥


በዚህን ጊዜ ንግሥቲቱ በንጉሠ ነገሥቱ አጠገብ ተቀምጣ ነበር፤ ንጉሠ ነገሥቱም ጥያቄዬን በመቀበል፦ “ጒዞህ ምን ያኽል ጊዜ ይወስድብሃል? እስከ መቼስ ትመለሳለህ?” ብሎ ጠየቀኝ። እኔም የሚወስድብኝን ጊዜና መቼ እንደምመለስ ነገርኩት።


ንጉሥ ሆይ! እንግዲህ መልካም ፈቃድህ ቢሆን፥ ንግሥት አስጢን ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አንተ ፊት መቅረብ ከቶ እንዳይፈቀድላት የሚገልጥ ውሳኔህን በዐዋጅ አስተላልፍ፤ ይህም ውሳኔ ከቶ የማይለወጥ ሆኖ ለዘለዓለም ይጸና ዘንድ በፋርስና በሜዶን ሕግ ውስጥ እንዲመዘገብ ትእዛዝ አስተላልፍ፤ የአስጢንንም የንግሥትነት ማዕርግ ከእርስዋ ለተሻለች ለሌላ ሴት ስጥ።


አስቴርም “ንጉሥ ሆይ! በፊትዎ ሞገስ አግኝቼ ከሆነና በትሕትና የማቀርብልዎትን ጥያቄ ሊቀበሉኝ መልካም ፈቃድዎ ከሆነ፥ የእኔ ፍላጎት እኔም ሆንኩ ወገኖቼ በሕይወት መኖር እንድንችል ነው፤


“የግርማዊነትዎ መልካም ፈቃድ ቢሆንና ስለ እኔም የሚያስብልኝ ከሆነ፥ እንዲሁም ጉዳዩ በእርስዎ ፊት ትክክል ሆኖ ከተገኘ፥ በንጉሠ ነገሥት ግዛትዎ ሁሉ ውስጥ የሚገኙ አይሁድ ሁሉ ይደመሰሱ ዘንድ የአጋግ ዘር የነበረው የሃመዳታ ልጅ ሃማን ሰጥቶት የነበረውን ትእዛዝ ሁሉ የሚሽር ዐዋጅ እንዲያስተላልፉልኝ እለምንሃለሁ።


ይህን ብታደርግ በእግዚአብሔርና በሰው ፊት መወደድንና መልካም ዝናን ታገኛለህ።


ይህን ልብ ብለህ አስተውል፤ ኢየሩሳሌም እንድትታደስ ትእዛዝ ከወጣበት ጊዜ አንሥቶ መሲሕ እስከሚመጣበት ጊዜ ድረስ ሰባት ሳምንቶች ያልፋሉ፤ እንዲሁም ለሥልሳ ሁለት ሳምንት በችግር ጊዜ ኢየሩሳሌም፥ መንገዶችዋና የመከላከያ ጒድጓድዋ ይገነባሉ። ይሁን እንጂ ይህ ሁሉ የመከራ ዘመን ይሆናል።


“እናንተ ግብዞች የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን! ወዮላችሁ! በውስጣቸው በሞቱ ሰዎች አጥንትና በርኩስ ነገር ሁሉ የተሞሉ፥ በውጪ ግን በኖራ ተለስነው የሚያምሩ መቃብሮችን ትመስላላችሁ።


ሩትም “ጌታዬ ሆይ! ምንም እንኳ ከአገልጋዮችህ እንደ አንዲቱ ባልሆን እኔን አገልጋይህን በመልካም ቃላት አጽናንተኸኛል፤ ይህ በፊትህ ያገኘሁት ሞገስ እንዲቀጥል ፍቀድልኝ!” አለችው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos