ናሆም 3:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ነነዌ ሆይ! አንቺም የውሃ መከላከያ እንዳለሽ ሁሉ በአባይ ወንዝ አጠገብ ከነበረችው፥ ዙሪያዋ በውሃ ከተከበበው፥ የባሕር ውሃም መከላከያዋ ከሆነው ከግብጽ ከተማ ከቴብስ ትበልጫለሽን? Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 አንቺ በአባይ ወንዝ አጠገብ ካለችው፣ በውሃ ከተከበበችው፣ ከኖእ አሞን ትበልጫለሽን? ወንዙ መከላከያዋ፣ ውሃውም ቅጥሯ ነው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 አንቺ በዓባይ ፈሳሾች መካከል ከተቀመጠችው፥ ውኃም በዙሪያዋ ከነበራት፥ ምሽግዋም ባሕር ከነበረ፥ ቅጥርዋም በባሕር ውስጥ ከነበረ ከኖእ አሞን ትበልጫለሽን? Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 አንቺ በመስኖች መካከል ከተቀመጠችው፥ ውኃም በዙሪያዋ ከነበራት፥ ምሽግዋም ባሕር ከነበረ፥ ቅጥርዋም በባሕር ውስጥ ከነበረ ከኖእ አሞን ትበልጫለሽን? Ver Capítulo |
ከጽዋው መጠጣት የሚገባቸው ሌሎች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፦ የግብጽ ንጉሥ ከባለሟሎቹና ከመኳንንቱ ሁሉ ጋር፥ የግብጽ ሕዝብና በግብጽ የሚኖሩ መጻተኞች ሁሉ፥ በዑፅ ምድር የሚኖሩ ነገሥታት ሁሉ፥ በፍልስጥኤማውያን ከተሞች፥ በአስቀሎና፥ በጋዛ፥ በዔቅሮንና በአሽዶድ፥ በሌሎች ቦታዎችም የሚኖሩ የኤዶም፥ የሞአብና የዐሞን ሕዝቦች ሁሉ፥ የጢሮስና የሲዶና ነገሥታት ሁሉ፥ በሜዲትራኒያን ባሕር ዙሪያ በሚገኙ አገሮች ያሉ ነገሥታት ሁሉ፥ የደዳን፥ የቴማና የቡዝ ከተሞች ሁሉ፥ የግንባራቸውን ግራና ቀኝ ጠጒር የሚላጩ ሕዝቦች ሁሉ፥ የዐረብ አገር ነገሥታት ሁሉ፥ በበረሓ የሚኖሩ ነገዶች ነገሥታት ሁሉ፥ የዘምሪ፥ የዔላምና የሜዶን ነገሥታት ሁሉ፥ ሌሎችም በስተሰሜን በኩል በሩቅና በቅርብ ያሉ ነገሥታት ሁሉ በየተራቸው። በምድር ላይ የሚኖሩት ሕዝብ ሁሉ፥ ከዚህ ጽዋ ይጠጣሉ፤ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ከዚህ ጽዋ መጠጣት ይኖርበታል።