Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማቴዎስ 5:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ባላጋራህ ከሶህ ከእርሱ ጋር ወደ ፍርድ ቤት ስትሄድ በመንገድ ላይ ሳለህ ቶሎ ብለህ ከባላጋራህ ጋር ተስማማ። አለበለዚያ ባላጋራህ ለዳኛ፥ ዳኛውም ለአሳሪ አሳልፎ ይሰጥህና ወደ ወህኒ ቤት ትገባለህ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “የከሰሰህ ባላጋራህ እንዳያስፈርድብህ፣ ዳኛውም ለአገልጋዩ አሳልፎ እንዳይሰጥህ፣ ወደ ወህኒ እንዳትጣል፣ በመንገድ ላይ ሳለህ ከባላጋራህ ጋራ ፈጥነህ ተስማማ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ባላጋራህ ለዳኛ፥ ዳኛውም ለሎሌው እንዳይሰጥህ ወደ እስር ቤት እንዳትገባ፤ ከባላጋራህ ጋር በመንገድ አብረኸው ስትሄድ ሳለህ ፈጥነህ ተስማማ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 አብረኸው በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ፈጥነህ ተስማማ፤ ባላጋራ ለዳኛ እንዳይሰጥህ ዳኛም ለሎሌው፤ወደ ወህኒም ትጣላለህ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 አብረኸው በመንገድ ሳለህ ከባላጋራህ ጋር ፈጥነህ ተስማማ፤ ባላጋራ ለዳኛ እንዳይሰጥህ ዳኛም ለሎሌው፥ ወደ ወህኒም ትጣላለህ፤

Ver Capítulo Copiar




ማቴዎስ 5:25
19 Referencias Cruzadas  

አንተ ከመሰከርክ በኋላ ሌላ ሰው ምስክርነትህ የተሳሳተ መሆኑን የገለጠ እንደሆን ስለምታፍር ስለ አየኸው ነገር ለመመስከር ፈጥነህ ወደ ሸንጎ አትሂድ።


ይልቅስ ከእናንተ በኃጢአት ተታሎ ልቡን እምቢተኛ እንዳያደርግ “ዛሬ” ተብሎ የተጠራው ጊዜ እስካለ ድረስ በየቀኑ ተመካከሩ።


ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሚለው “ዛሬ ድምፁን ስትሰሙ


በኋላም ዔሳው በረከትን እንደገና ለመቀበል በፈለገ ጊዜ ይህን በረከት እንደ ተከለከለ ታውቃላችሁ፤ እያለቀሰ እንኳ ያንን በረከት ተግቶ ቢፈልግ ሊያገኘው አልቻለም። ለንስሓ ምንም ዕድል አላገኘም።


“ስለዚህ ኢዮብ ሆይ፥ ራስህን ለእግዚአብሔር አስገዛ፤ ከእርሱም ጋር ሰላም ይኑርህ፤ ይህን ብታደርግ መልካም ነገርን ታገኛለህ።


እግዚአብሔር፦ “ተስማሚ በሆነ ጊዜ ሰማሁህ! በመዳን ቀን ረዳሁህ!” ስለሚል፥ “እነሆ ተስማሚ የሆነው ጊዜ አሁን ነው፤ የመዳኛው ቀን አሁን ነው።”


ስለዚህ በጭንቀት ሰዓት እያንዳንዱ ለአንተ ታማኝ ሰው ወደ አንተ ይጸልይ፤ ብርቱ የመከራ ጐርፍ በሚመጣበት ጊዜ እርሱን አይነካውም።


ጴጥሮስ ግን እስከ ካህናት አለቃው ግቢ ድረስ ኢየሱስን በሩቅ ተከተለው፤ ወደ ውስጥ ገብቶም የነገሩን ፍጻሜ ለማየት ከዘበኞች ጋር ተቀመጠ።


አንዲት መበለትም በዚያች ከተማ ትኖር ነበር፤ እርስዋ ወደ ዳኛው እየመጣች ‘ከባላጋራዬ ጋር ስላለኝ ክርክር ፍርድ ስጠኝ!’ ትለው ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios