Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማርቆስ 8:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ከዚያም በኋላ ኢየሱስ “ወደ መንደሩ አትግባ፤” ብሎ ወደ ቤቱ እንዲሄድ አሰናበተው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ከዚያም፣ “ወደ መንደሩ አትግባ! በመንደሩም ለማንም አትናገር” ብሎ ወደ ቤቱ ሰደደው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ከዚያም፥ “ወደ መንደሩ አትግባ በመንደሩም ለማንም አትናገር” ብሎ ወደ ቤቱ ላከው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ወደ ቤቱም ሰደደውና “ወደ መንደሩ አትግባ፤ በመንደሩም ለማንም አንዳች አትናገር፤” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ወደ ቤቱም ሰደደውና፦ ወደ መንደሩ አትግባ በመንደሩም ለማንም አንዳች አትናገር አለው።

Ver Capítulo Copiar




ማርቆስ 8:26
7 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፥ ከለምጹ የዳነውን ሰው እንዲህ አለው፤ “ይህን ነገር ለማንም አትናገር፤ ነገር ግን ሄደህ መዳንህን ለካህን አሳይ፤ ምስክር ይሆንባቸው ዘንድ፥ ስለ መዳንህ ሙሴ ያዘዘውን መባ ለእግዚአብሔር አቅርብ” አለው።


እርሱም ማየት የተሳነውን ሰው እጅ ይዞ እየመራ ከመንደር ወደ ውጪ አወጣው፤ በሰውየውም ዐይኖች ላይ ምራቁን እንትፍ ብሎ እጁን ጫነበትና “አንዳች ነገር ታያለህን?” ሲል ጠየቀው።


ኢየሱስ ይህን ነገር ለማንም እንዳይናገሩ ሰዎቹን አዘዛቸው፤ ይሁን እንጂ፥ እንዳይናገሩ ባዘዛቸው መጠን በብዙ አብልጠው ያወሩ ነበር።


ኢየሱስ ግን ይህን ነገር ማንም እንዳያውቅ አዘዛቸውና “የምትበላውን ስጡአት!” አላቸው።


ሰዎቹን ግን ስለ እርሱ ለማንም እንዳይናገሩ አዘዛቸው፤


ዐይኖቻቸውም ተከፈቱ፤ ኢየሱስም “ይህን ነገር ለማንም አትንገሩ!” ሲል በጥብቅ አዘዛቸው።


እንደገናም ኢየሱስ በሰውየው ዐይኖች ላይ እጁን ጫነ፤ በዚህ ጊዜ ሰውየው ትኲር ብሎ አየ፤ ድኖም ሁሉን ነገር አጥርቶ ማየት ጀመረ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios