Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማርቆስ 4:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 በዚያኑ ቀን ማታ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፦ “ወደ ባሕሩ ማዶ እንሻገር” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ያ ቀን በመሸ ጊዜ፣ “ወደ ማዶ እንሻገር” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 በዚያም ቀን በመሸ ጊዜ “ወደ ማዶ እንሻገር፤” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 በዚያም ቀን በመሸ ጊዜ “ወደ ማዶ እንሻገር፤” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 በዚያም ቀን በመሸ ጊዜ፦ ወደ ማዶ እንሻገር አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ማርቆስ 4:35
11 Referencias Cruzadas  

ኢየሱስ፥ ብዙ ሰዎች በዙሪያው ተሰብስበው ባየ ጊዜ ወደ ባሕሩ ማዶ እንዲሻገሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዘ።


ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፥ “እምነታችሁ የት አለ?” አላቸው። እነርሱ ግን እጅግ ተደንቀውና ፈርተው እርስ በርሳቸው፥ “ነፋስንና ማዕበልን ያዛል፤ እነርሱም ይታዘዙለታል፤ ለመሆኑ ይህ ማን ነው?” ተባባሉ።


አንድ ቀን ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በጀልባ ተሳፈረና “ወደ ባሕሩ ማዶ እንሻገር፤” አላቸው፤ እነርሱም ለመሄድ ተነሡ።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፥ “እኔ ሕዝቡን እስካሰናብት ድረስ በጀልባ ተሳፈሩና ቀድማችሁኝ ወደ ማዶ ተሻገሩ፤” ሲል አዘዛቸው።


ትቶአቸውም እንደገና በጀልባ ሆኖ ወደ ማዶ ተሻገረ።


ከባሕሩ ማዶ ባገኙትም ጊዜ፥ “መምህር ሆይ፥ ወደዚህ መቼ መጣህ?” አሉት።


በጀልባ ተሳፍረው ወደ ቅፍርናሆም አመሩ፤ በዚያን ሰዓት ጊዜው ጨልሞ ነበር፤ ኢየሱስም ገና ወደ እነርሱ አልመጣም ነበር።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ጥብርያዶስ ወደሚባለው ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ተሻገረ።


ኢየሱስ ወዲያውኑ ሕዝቡን ሲያሰናብት ሳለ ደቀ መዛሙርቱ በጀልባ ሆነው ወደ ማዶ ወደ ቤተ ሳይዳ ተሻግረው እንዲቀድሙት አዘዛቸው።


ኢየሱስ በጀልባ ወደ ባሕሩ ማዶ እንደገና በተመለሰ ጊዜ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ በዚያ ጊዜ እርሱ በባሕሩ አጠገብ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios