Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ማርቆስ 3:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 አንድ መንግሥት ተከፋፍሎ እርስ በርሱ የሚጋጭ ከሆነ ያ መንግሥት ጸንቶ መቆም አይችልም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 እርስ በርሱ የሚከፋፈል መንግሥት ሊጸና አይችልም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 መንግሥትም እርስ በርስዋ ከተለያየች ያች መንግሥት ልትቆም አትችልም፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 መንግሥትም እርስ በርስዋ ከተለያየች ያች መንግሥት ልትቆም አትችልም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 መንግሥትም እርስ በርስዋ ከተለያየች ያች መንግሥት ልትቆም አትችልም፤

Ver Capítulo Copiar




ማርቆስ 3:24
15 Referencias Cruzadas  

በዚያን ጊዜ ሼባዕ ተብሎ የሚጠራ ጠባዩ የተበላሸ የማይረባ አንድ ሰው በጌልገላ ይኖር ነበር፤ እርሱም ትውልዱ ከብንያም ነገድ ሲሆን አባቱ ቢክሪ ይባላል፤ ይህም ሼባዕ እምቢልታ ነፍቶ “ከዳዊት ጋር ምንም ድርሻ የለንም! ከእሴይ ልጅ ጋር ምንም ዕድል ፈንታ የለንም! የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! እያንዳንድህ ወደ ቤትህ ግባ!” ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ።


ስለዚህ ንጉሡ አቢሳን “ሼባዕ ከአቤሴሎም ይበልጥ የከፋ ችግር ይፈጥርብናል፤ ወታደሮቼን ይዘህ ተከታተለው፤ አለበለዚያ የተመሸጉ ከተሞቼን ይዞ ከእኛ እጅ ሊያመልጥ ይችላል” አለው።


በእስራኤል ምድርና በተራሮችዋ አንድ መንግሥት እንዲሆኑ አደርጋለሁ፤ ሁሉንም በአንድነት የሚያስተዳድር አንድ ንጉሥ ይኖራቸዋል፤ ዳግመኛ ሁለት ሕዝብ አይሆኑም፤ መንግሥታቸውም በሁለት አይከፈልም።


ከዚህ በኋላ “አንድነት” የተባለውን ሁለተኛውን በትር ሰበርኩት፤ ይህንንም ማድረጌ በይሁዳና በእስራኤል መካከል የነበረው ወንድማማችነት መጥፋቱን ለማመልከት ነበር።


ኢየሱስም ሐሳባቸውን ዐውቆ እንዲህ አላቸው፦ “አንድ መንግሥት ተከፋፍሎ እርስ በእርሱ የሚጋጭ ከሆነ፥ ያ መንግሥት ይወድቃል። እንዲሁም አንድ ከተማ ወይም አንድ ቤተሰብ እርስ በርሱ ከተለያየ ጸንቶ መኖር አይችልም።


ኢየሱስም እነርሱን ወደ እርሱ ጠርቶ በምሳሌ እንዲህ አላቸው፦ “ሰይጣን እንዴት ሰይጣንን ሊያስወጣ ይችላል?


እንዲሁም አንድ ቤተሰብ እርስ በርሱ ከተለያየ ጸንቶ መኖር አይችልም፤


እኔም የምለምነው ሁሉም አንድ እንዲሆኑ ነው፤ እንዲሁም አባት ሆይ! አንተ በእኔ እንዳለህ፥ እኔም በአንተ እንዳለሁ፥ እነርሱም በእኛ እንዲኖሩ ነው፤ አንተ እንደ ላክኸኝም ዓለም እንዲያምን ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos