Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማርቆስ 14:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ነገር ግን ሕዝቡ ሁከት ያነሣሣል በማለት “በበዓል ቀን ይህን አናደርግም፤” አሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ሆኖም፣ “ሕዝቡ ዐመፅ እንዳያነሣ በበዓሉ ሰሞን መሆን የለበትም” ይባባሉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ሆኖም፥ “ሕዝቡ ዐመፅ እንዳያነሣ በበዓሉ ሰሞን መሆን የለበትም” ይባባሉ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “የሕዝብ ሁከት እንዳይሆን በበዓል አይሁን፤” ይሉ ነበርና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የሕዝብ ሁከት እንዳይሆን በበዓል አይሁን ይሉ ነበርና።

Ver Capítulo Copiar




ማርቆስ 14:2
13 Referencias Cruzadas  

በዚህ ጊዜ ፈሪሳውያን፥ “እነሆ፥ የዓለም ሕዝብ ሁሉ ተከትሎታል! እኛ ምንም ማድረግ እንደማንችል ታያላችሁን?” ተባባሉ።


ስለዚህ ከሕዝቡ አንዳንዶቹ ይህን ቃል በሰሙ ጊዜ፦ “ይመጣል የተባለው ነቢይ በእርግጥ ይህ ነው” አሉ።


‘ከሰው ነው’ ብንል ደግሞ ሕዝቡ ሁሉም በዮሐንስ ነቢይነት ስለሚያምኑ በድንጋይ ይወግሩናል።”


‘ከሰው ነው፥’ ብንልሳ?” ይህን እንዳይሉ ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን በእርግጥ ነቢይ ነው ይሉ ስለ ነበር ፈሩ።


የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ይህን ሲናገር ሰሙት፤ ሕዝቡም ሁሉ በትምህርቱ ይደነቁ ስለ ነበር ፈሩት፤ ስለዚህ እንዴት አድርገው እንደሚያጠፉት ዘዴ ይፈልጉ ነበር።


ነገር ግን “በሕዝቡ መካከል ሁከት እንዳይነሣ በበዓል ቀን አይሁን” አሉ።


ሰው በወጣትነቱ መከራን በትዕግሥት ቢቀበል መልካም ነው።


ሰው በጥበቡ፥ በአስተዋይነቱና በዕቅዱ በእግዚአብሔር ላይ መነሣት አይችልም።


ሰዎች ብዙ ነገር ያቅዳሉ፤ ተፈጻሚነትን የሚያገኘው ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው።


“ከሁለት ቀን በኋላ የፋሲካ በዓል እንደሚሆን ታውቃላችሁ፤ የሰው ልጅ ለመሰቀል ተላልፎ ይሰጣል።”


የአይሁድ የፋሲካና የቂጣ በዓል ሊከበር ሁለት ቀን ቀርቶት ነበር፤ የካህናት አለቆችና የሕግ መምህራን ኢየሱስን በተንኰል ይዘው የሚገድሉበትን ዘዴ ይፈልጉ ነበር።


ኢየሱስ በቢታንያ ለምጻም በነበረው በስምዖን ቤት ነበር። በገበታም ቀርቦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ ውድ የሆነና የከበረ የናርዶስ ሽቶ የሞላበት፥ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች፤ ብልቃጡን ሰብራ ሽቶውን በኢየሱስ ራስ ላይ አፈሰሰችው።


ፋሲካ የተባለው የቂጣ በዓል የሚከበርበት ቀን ተቃርቦ ነበር፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios