Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ማርቆስ 14:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በገበታ ቀርበው ሲበሉ ኢየሱስ “በእውነት እላችኋለሁ፤ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል፤ እርሱም አሁን ከእኔ ጋር ራት በመብላት ላይ የሚገኘው ነው፤” አለ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 በማእድ ላይ ሳሉም፣ “እውነት እላችኋለሁ፣ ከመካከላችሁ አንዱ፣ ዐብሮኝ የሚበላው እርሱ አሳልፎ ይሰጠኛል” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በማእድ ላይ ሳሉም፥ “እውነት እላችኋለሁ፥ ከመካከላችሁ አንዱ፥ አብሮኝ የሚበላው እርሱ አሳልፎ ይሰጠኛል” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ተቀምጠውም ሲበሉ ኢየሱስ “እውነት እላችኋለሁ፥ ከእናንተ አንዱ፥ እርሱም ከእኔ ጋር የሚበላው አሳልፎ ይሰጠኛል፤” አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ተቀምጠውም ሲበሉ ኢየሱስ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከእናንተ አንዱ፥ እርሱም ከእኔ ጋር የሚበላው አሳልፎ ይሰጠኛል አለ።

Ver Capítulo Copiar




ማርቆስ 14:18
36 Referencias Cruzadas  

እንጀራዬን ከእኔ ጋር አብሮ የበላ ከልብ የምተማመንበት ወዳጄ እንኳ በእኔ ላይ በጠላትነት ተነሥቶአል።


ኢየሱስም “እናንተን ዐሥራ ሁለታችሁን መርጬአችሁ የለምን? ነገር ግን ከእናንተ አንዱ ዲያብሎስ ነው” አላቸው።


እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ (በእኔ) የሚያምን ሰው የዘለዓለም ሕይወት አለው።


ኢየሱስም “አንተ ሕይወትህን ስለ እኔ አሳልፈህ ትሰጣለህን? እውነት፥ እውነት እልሃለሁ፤ ዛሬ ዶሮ ከመጮሁ በፊት ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ” ሲል መለሰ።


ኢየሱስ ይህን ካለ በኋላ በመንፈሱ ተጨነቀና “እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ ከእናንተ አንዱ አሳልፎ ይሰጠኛል” ሲል ገልጦ ተናገረ።


በዚህ ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ ከሰማይ የወረደውን እንጀራ የሰጣችሁ ሙሴ አይደለም፤ እውነተኛውን እንጀራ ከሰማይ የሚሰጣችሁ አባቴ ነው፤


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ እናንተ የምትፈልጉኝ እንጀራ ስለ በላችሁና ስለ ጠገባችሁ ነው እንጂ ተአምራት ስላያችሁ አይደለም።


ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ አብ ሲሠራ ያየውን ከመሥራት በቀር ወልድ በራሱ ሥልጣን ምንም ሊሠራ አይችልም። አብ የሚያደርገውን ወልድም እንዲሁ ያደርጋል።


እውነት፥ እውነት እልሃለሁ፤ የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሰክራለን፤ እናንተ ግን ምስክርነታችንን አትቀበሉትም።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “እውነት፥ እውነት እልሃለሁ፤ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።


ኢየሱስም “እውነት፥ እውነት እልሃለሁ፤ ሰው እንደገና ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም” አለው።


እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፦ ሰማይ ሲከፈት የእግዚአብሔር መላእክትም በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያላችሁ።”


በእርግጥ እነግራችኋለሁ፤ ከአቤል ጀምሮ በመሠዊያውና በቤተ መቅደሱ መካከል እስከ ተገደለው እስከ ዘካርያስ ድረስ ስለ ፈሰሰው ደም ይህ ትውልድ በፍርድ ይጠየቅበታል።


በእውነት እላችኋለሁ፤ ነቢይ በገዛ አገሩ ሰዎች ዘንድ አይከበርም።


በእውነት እላችኋለሁ፤ በእግዚአብሔር መንግሥት ከአዲሱ ወይን እስክጠጣ ድረስ ከዚህ ወይን ፍሬ ጭማቂ ዳግመኛ አልጠጣም።”


በእውነት እላችኋለሁ፤ በዓለም ሁሉ ይህ ወንጌል በሚሰበክበት በማናቸውም ስፍራ፥ ይህ እርስዋ ያደረገችው ለመታሰቢያ ይነገርላታል።”


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “በእውነት እላችኋለሁ፤ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ብሎ ቤትን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም እናትን ወይም አባትን ወይም ልጆችን ወይም ርስትን የሚተው ሰው ይበልጥ ያገኛል፤


በእውነት እላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደ ሕፃን ሆኖ የማይቀበላት ከቶ አይገባባትም።”


በእውነት እላችኋለሁ፤ የክርስቶስ ስለ ሆናችሁ በስሜ አንድ ብርጭቆ ውሃ እንኳ የሚያጠጣቸው ዋጋውን አያጣም፤” አላቸው።


ቀጥሎም ኢየሱስ፦ “በእውነት እላችኋለሁ፤ አሁን እዚህ ካሉት መካከል አንዳንዶች የእግዚአብሔር መንግሥት በታላቅ ኀይል ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ የማይሞቱ አሉ፤” አላቸው።


ኢየሱስ በመንፈሱ በመቃተት፦ “የዚህ ዘመን ትውልድ ተአምር እንዲደረግለት ስለምን ይፈልጋል? በእውነት እላችኋለሁ፤ ለዚህ ትውልድ ምንም ተአምር አይደረግለትም!” አላቸው።


ሰዎች በማይቀበሉአችሁና በማይሰሙአችሁ ቦታ ሁሉ የእግራችሁን አቧራ አራግፉና ከዚያ ወጥታችሁ ሂዱ፤ ይህም ለእነርሱ የማስጠንቀቂያ ምስክር ይሆንባቸዋል።”


“በእውነት እላችኋለሁ፤ ሰዎች የሚሠሩት ኃጢአትና የሚናገሩት ስድብ ሁሉ ይቅር ይባልላቸዋል።


ሲበሉም ኢየሱስ፦ “በእውነት እላችኋለሁ፤ ከእናንተ አንዱ እኔን አሳልፎ ይሰጣል” አለ።


“በምትጸልዩበት ጊዜ እንደ ግብዞች አትሁኑ! እነርሱ ሰው እንዲያይላቸው ብለው በየምኲራቡና በየመንገዱ ዳር ቆመው መጸለይ ይወዳሉ። በእውነት እላችኋለሁ፥ እነርሱ ዋጋቸውን በቅድሚያ አግኝተዋል።


ስለዚህ ለድኾች ምጽዋት በምትመጸውትበት ጊዜ፥ ግብዞች በየምኲራቡና በየመንገዱ እንደሚያደርጉት ለታይታ አታድርጉ፤ በእውነት እነግራችኋለሁ፥ እነርሱ ዋጋቸውን አስቀድመው አግኝተዋል።


በእውነት እላችኋለሁ፤ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ ሕግ ሁሉ ይፈጸማል እንጂ ከሕግ አንዲት ጭረት ወይም አንዲት ነጥብ አትሻርም።


እውነት፥ እውነት እልሃለሁ፤ አንተ ጐልማሳ ሳለህ ቀበቶህን በገዛ እጅህ ታጥቀህ ወደ ፈለግኽበት ትሄድ ነበር፤ በሸመገልክ ጊዜ ግን አንተ እጆችህን ትዘረጋና ሌላ ሰው ያስታጥቅሃል፤ ወደማትፈልግበትም ይወስድሃል።”


ኢየሱስም ቀጥሎ እንዲህ አለ፦ “በምትጾሙበት ጊዜ፥ መጾማቸውን ሰዎች እንዲያውቁላቸው፥ ፊታቸውን እንደሚለውጡት እንደ ግብዞች፥ ፊታችሁን አታጠውልጉ፤ በእውነት እላችኋለሁ፥ እነርሱ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።


በመሸ ጊዜ ኢየሱስ ከዐሥራ ሁለቱ ጋር መጣ፤


እነርሱም በዚህ ነገር አዝነው “እኔ እሆንን?” እያሉ ተራ በተራ ጠየቁት።


“ነገር ግን አሳልፎ የሚሰጠኝ ሰው እጅ እነሆ፥ ከእኔ ጋር በማእድ ነው።


ይህን የምናገረው ስለ ሁላችሁም አይደለም፤ እኔ የመረጥኳችሁን ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ‘እንጀራዬን የበላ በእኔ ላይ በጠላትነት ተነሣብኝ’ የሚለው የቅዱስ መጽሐፍ ቃል መፈጸም አለበት።


ደቀ መዛሙርቱ ይህን ስለ ማን እንደ ተናገረ ባለማወቃቸው እርስ በእርሳቸው ተያዩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios