Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ማርቆስ 12:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 “እንግዲህ የወይኑ ተክል ጌታ ምን ያደርጋል? ባለቤቱ ራሱ ይመጣል፤ ገበሬዎቹንም ይገድላል፤ የወይኑንም ተክል ለሌሎች ይሰጣል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “እንግዲህ የወይኑ አትክልት ባለቤት ምን የሚያደርግ ይመስላችኋል? ይመጣል፤ ገበሬዎቹን ይገድላል፤ የወይኑንም አትክልት ለሌሎች ይሰጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እንግዲህ የወይኑ አትክልት ባለቤት ምን የሚያደርግ ይመስላችኋል? ይመጣል፤ ገበሬዎቹን ይገድላል፤ የወይኑንም አትክልት ለሌሎች ይሰጣል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እንግዲህ የወይኑ አትክልት ጌታ ምን ያደርጋል? ይመጣል፤ ገበሬዎቹንም ያጠፋል፤ የወይኑንም አትክልት ለሌሎች ይሰጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እንግዲህ የወይኑ አትክልት ጌታ ምን ያደርጋል? ይመጣል ገበሬዎቹንም ያጠፋል፥ የወይኑንም አትክልት ለሌሎች ይሰጣል።

Ver Capítulo Copiar




ማርቆስ 12:9
33 Referencias Cruzadas  

በጥቂት ጊዜ ውስጥ የሊባኖስ ጫካ የእርሻ ቦታ ይሆናል፤ የእርሻው ቦታ ወደ ጫካነት ይለወጣል።


እኔ ጌታ እግዚአብሔርም እናንተን ለሞት አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ የእናንተም ስም በእኔ ተመራጮች ዘንድ መራገሚያ ይሆናል፤ ለአገልጋዮቼ ግን የተለየ ስም እሰጣቸዋለሁ።


በመላ አገራችሁ በፈጸማችሁት ከፍተኛ ኃጢአት ምክንያት ያላችሁን ሀብትና ንብረት እንዲሁም መሠዊያዎቻችሁን ሁሉ በምርኮ ጠላቶቻችሁ እንዲወስዱ አደርጋለሁ።


እነሆ፥ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ዳር እስከ ዳር ለእኔ ክብር ይሰጣሉ፤ በየትኛውም ስፍራ ለእኔ ዕጣን እያጠኑ ንጹሕ መሥዋዕት ያቀርቡልኛል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ያከብሩኛል።


ከዚህ በኋላ፥ ርኩሱ መንፈስ ይሄድና ከእርሱ ይብስ የከፉትን ሌሎች ሰባት አጋንንት ይዞ ይመጣል። እነርሱም ቀድሞ የጋኔኑ ቤት ወደ ነበረው ሰው ልብ ገብተው አብረው በዚያ ይኖራሉ። ስለዚህ የዚያ ሰው የኋለኛው ሁኔታ ከመጀመሪያው ይልቅ የከፋ ይሆናል። በዚህ ክፉ ትውልድ ላይ የሚሆነው ይህንኑ የመሰለ ነገር ነው።”


የፍሬ ወራት በደረሰ ጊዜ ድርሻውን እንዲቀበሉለት አገልጋዮቹን ወደ ገበሬዎቹ ላከ።


“ስለዚህ እንዲህ እላችኋለሁ፤ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ተወስዳ ፍሬ ለሚያፈራ ሕዝብ ትሰጣለች። [


በዚህ ጊዜ ንጉሡ ተቈጣና ወታደሮቹን ልኮ እነዚያን ገዳዮች አስገደለ፤ ከተማቸውንም በእሳት እንዲያቃጥሉ አደረገ፤


ለመሆኑ፥ ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ የማእዘን ራስ ሆነ፤


ስለዚህ ልጁን ይዘው ገደሉት፤ ከወይኑ ተክልም ቦታ ውጪ ጣሉት።


በእነርሱ ላይ እንድነግሥ ያልፈለጉትን እነዚያን ጠላቶቼን ግን እዚህ አምጥታችሁ በፊቴ ግደሉአቸው!’ ” አላቸው።


ኢሳይያስም፦ “ላልፈለጉኝ ተገኘሁ፤ ‘እግዚአብሔር የት ነው?’ ብለው ላልጠየቁኝም ተገለጥሁ፤” በማለት ደፍሮ ተናግሮአል።


አምላካችሁ እግዚአብሔር የተናገረውን መልካም ነገር ሁሉ እንደ ፈጸመላችሁ፥ እንዲሁም እርሱ ከሰጣችሁ ከዚህች መልካም ምድር እስኪያጠፋችሁ ድረስ ክፉን ነገር ሁሉ ሊያመጣባችሁ ይችላል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos