Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 5:25 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ሽባውም በሰዎቹ ፊት ወዲያው ተነሣና፥ ተኝቶበት የነበረውን አልጋ ተሸክሞ፥ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ ቤቱ ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 እርሱም ወዲያው ተነሥቶ በፊታቸው ቆመ፤ ተኝቶበት የነበረውንም ተሸክሞ፣ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ ቤቱ ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ወዲያውኑ በፊታቸው ተነሣ፤ ተኝቶበትም የነበረውን ተሸክሞ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ ቤቱ ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ያን​ጊ​ዜም ተነ​ሥቶ ተኝ​ቶ​በት የነ​በ​ረ​ውን አልጋ በፊ​ታ​ቸው ተሸ​ክሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እያ​መ​ሰ​ገነ ወደ ቤቱ ሄደ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በዚያን ጊዜም በፊታቸው ተነሣ፥ ተኝቶበትም የነበረውን ተሸክሞ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ ቤቱ ሄደ።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 5:25
12 Referencias Cruzadas  

በዚህ ምክንያት ዕውር የነበረውን ሰው እንደገና ጠርተው “አንተ እውነቱን በመናገር እግዚአብሔርን አክብር፤ ይህ ሰው ኃጢአተኛ መሆኑን እኛ እናውቃለን” አሉት።


ዐይነ ስውሩም ወዲያውኑ ማየት ቻለ፤ እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ኢየሱስን መከተል ጀመረ፤ ሕዝቡም ሁሉ ይህን ባዩ ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።


እጆቹን ጫነባት፤ ወዲያውም ቀጥ ብላ ቆመች፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነች።


ኢየሱስም እጁን ዘርግቶ ዳሰሰውና “ፈቅጃለሁ ንጻ!” አለው። ሰውዬውም ወዲያውኑ ከለምጹ ነጻ።


የምስጋና መሥዋዕት የሚያቀርብልኝ ያከብረኛል፤ መንገዴን ለሚከተል አዳኝነቴን አሳየዋለሁ።”


እርሱ በተናገረ ጊዜ ዓለም ተፈጠረ፤ በትእዛዙም ሁሉ ነገር ጸንቶ ቆመ።


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር “ብርሃን ይሁን” አለ፤ ብርሃንም ሆነ።


ሕዝቡም ይህን ባዩ ጊዜ ተገረሙ፤ እንዲህ ያለውንም ሥልጣን ለሰው በመስጠቱ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።


ሽባውም ወዲያውኑ ተነሣና አልጋውን ተሸክሞ በሰዎቹ ሁሉ ፊት ወጣ። ስለዚህም ሰዎቹ ሁሉ ተደንቀው እንዲህ ያለ ነገር ከቶ አይተን አናውቅም እያሉ እግዚአብሔርን አመሰገኑ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios