Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 7:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ከአንድነቱ መሥዋዕት በቀኝ በኩል ያለው ወርች ድርሻው ሆኖ ለካህኑ ይሰጥ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 የኅብረት መሥዋዕታችሁን የቀኝ ወርች ለካህኑ የተለየ አድርጋችሁ ስጡት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ከሰላም መሥዋዕታችሁ ቀኝ ወርቹን እንደ ቁርባን አድርጋችሁ ለካህኑ ትሰጡታላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችሁ ቀኝ ወር​ቹን ለማ​ን​ሣት ቍር​ባን እን​ዲ​ሆን ለካ​ህኑ ትሰ​ጡ​ታ​ላ​ቸሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ከደኅንነት መሥዋዕታችሁ ቀኝ ወርቹን ለማንሣት ቁርባን እንዲሆን ለካህኑ ትሰጡታላችሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 7:32
12 Referencias Cruzadas  

“አሮንና ልጆቹ ከሚካኑበት አውራ በግ ተወስዶ ለመሥዋዕት የተወዘወዘውን ፍርምባና የተነሣውን ወርች ትቀድሳለህ። እርሱም ተመልሶ ለካህናቱ የሚመደብ ድርሻ ይሆናል።


ነገር ግን በመወዝወዝ ልዩ መባ ሆኖ ለእግዚአብሔር ከቀረበ በኋላ የካህናቱ ድርሻ እንዲሆን ስለ ተፈቀደ ፍርምባውንና ወርቹን አንተና ቤተሰብህ ሴቶች ልጆችህ ጭምር ትበሉታላችሁ፤ ይህንንም በተቀደሰ ስፍራ ትበሉታላችሁ፤ ይህም የእስራኤል ሕዝብ የአንድነት መሥዋዕት አድርገው ከሚያቀርቡት መባ ሁሉ ተከፍሎ ለአንተና ለልጆችህ ተሰጥቶአል።


የቀኙ ወርች የአንድነቱን መሥዋዕት ደምና ስብ ለሚያቀርበው ካህን ድርሻ ይሁን፤


ከእስራኤላውያን የአንድነት መሥዋዕት መካከል የተወዘወዘውን ፍርንባና የሚቀርበውን ወርች ከእስራኤላውያን እንደሚቀርብላቸው ቋሚ ድርሻ አድርጌ ለካህኑ ለአሮንና ለልጆቹ ሰጥቻቸዋለሁ።


ፍርምባዎቹንና በስተቀኝ በኩል ያሉትን የኋላ እግሮች ሙሴ ባዘዘው መሠረት በመወዝወዝ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጎ አቀረበው።


በዚህም ዐይነት እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት ልዩ ስጦታ ሁሉ ስጦታውን ለሚቀበለው ካህን ድርሻ ይሆናል።


ከዚህም በኋላ ካህኑ ይህን ሁሉ ወስዶ ለእግዚአብሔር የሚወዘወዝ ልዩ መባ አድርጎ ያቀርበዋል፤ ይህም ሁሉ የካህኑ ድርሻ ሆኖ ከሚነሣው ከአውራው በግ ፍርንባና ወርች ጋር ለካህኑ የተቀደሰ ድርሻ ይሆናል፤ ናዝራዊው የወይን ጠጅ መጠጣት የሚፈቀድለትም ከዚያን በኋላ ነው።


“የቀንድ ከብት ወይም በግ በሚሠዋበት ጊዜ ካህናቱ ወርቹን፥ አገጩንና፥ ጨጓራውን ይወስዳሉ።


ስለዚህም የወጥቤቱ ሠራተኛ ምርጥ የሆነውን የታናሽ ብልት ሥጋ አምጥቶ በሳኦል ፊት አስቀመጠ፤ ሳሙኤልም ሳኦልን “ተመልከት፤ ይህ ለአንተ ተለይቶ የተቀመጠልህ ምርጥ ሥጋ ነው፤ እኔ ከጋበዝኳቸው እንግዶች ጋር ሆነህ እንድትበላ ያስቀመጡልህ ስለ ሆነ እርሱን ተመገብ” አለው። ስለዚህም በዚያ ቀን ሳኦል ከሳሙኤል ጋር አብሮ ተመገበ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos