Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 6:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ለበደሉም ማስተስረያ ምንም ነውር የሌለበት አንድ ተባዕት በግ ወይም በታወቀው ተመን የተተመነውን ገንዘብ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቅርብ፤ እርሱንም አምጥቶ ለካህኑ ይስጥ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ከመንጋውም እንከን የሌለበትን ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ አውራ በግ ስለ በደሉ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ወደ ካህኑ ያምጣ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ተመጣጣኝ የሆነ ዋጋ ለበደል መሥዋዕት፥ ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ፥ ለጌታ ስለ በደሉ መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያመጣል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ስለ በደል መሥ​ዋ​ዕ​ትም ከመ​ን​ጋው ነውር የሌ​ለ​በ​ትን፥ ዋጋው እንደ በደሉ የተ​ገ​መ​ተ​ውን አውራ በግ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያምጣ።።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ስለ በደል መሥዋዕትም ለእግዚአብሔር ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ እንደ ግምጋሜህ መጠን ስለ በደል መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያምጣ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 6:6
8 Referencias Cruzadas  

እነርሱም ሚስቶቻቸውን ፈተው ለማሰናበት ቃል ከገቡ በኋላ ለኃጢአታቸው ማስተስረያ የሚሆን አንድ የበግ አውራ ለሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ።


የእህላችንን መከር በምንሰበስብበት ወቅትና የዛፎቻችንን ፍሬ በምንለቅምበት ወራት በመጀመሪያ የደረሰውን እሸት፥ ወደ ቤተ መቅደስ እያመጣን እናበረክታለን።


ወደ ሰሜን የሚያመለክተውም ክፍል በመሠዊያው ለማገልገል ኃላፊነት ለተሰጣቸው ካህናት ማረፊያ ነው፤ እነዚህ ሁሉ ካህናት ከሳዶቅ ዘር የተወለዱ ሌዋውያን ሲሆኑ፥ በፊቱ ቆመው እግዚአብሔርን ለማገልገል የተፈቀደላቸው እነርሱ ብቻ ናቸው።”


ከዚህም በኋላ ካህኑ ተባዕት ከሆኑት ከሁለቱ የበግ ጠቦቶች አንዱን የሊትር አንድ ሦስተኛ ከሆነው የወይራ ዘይት ጋር ወስዶ የበደል ስርየት መሥዋዕት አድርጎ ያቀርባል። ካህኑ ይህን በመወዝወዝ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጎ ያቀርበዋል።


“አንድ ሰው ለእግዚአብሔር መክፈል የሚገባውን ባለመክፈል ሳያውቅ በደል ቢፈጽም፥ ለእግዚአብሔር የበደል መሥዋዕት የሚሆን ከመንጋው ነውር የሌለበትን አውራ በግ ያምጣ፤ ወይም በቤተ መቅደሱ ሚዛን መሠረት ዋጋው ተገምግሞ ይክፈል። ይህም የበደል መሥዋዕት ነው።


ከመንጋው ምንም ነውር የሌለበት ተባዕት በግ ስለ በደሉ መሥዋዕት አድርጎ ወደ ካህን ያምጣ፤ ዋጋውም ተገምግሞ በይፋ በታወቀው ተመን ይወሰን፤ ካህኑም የእንስሳውን መሥዋዕት ስለዚያ ሰው ያቅርብ፤ በደል የሠራውም ሰው ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል።


“አንድ ሰው በግ ወይም ፍየል ማቅረብ ካልቻለ ግን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች፥ አንደኛይቱን ስለ ኀጢአት ለሚቀርብ መሥዋዕት፥ ሁለተኛይቱንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ የበደሉን ዕዳ ይከፍል ዘንድ ለእግዚአብሔር ያምጣ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos