Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 27:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 መሬቱን የኢዮቤልዩ ዓመት እንዳለፈ ወዲያውኑ ለይቶ የሰጠ ከሆነ ሙሉውን ዋጋ መክፈል ይኖርበታል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ሰውየው ዕርሻውን የቀደሰው በኢዮቤልዩ ዓመት ከሆነ፣ የተወሰነው ዋጋ አይለወጥም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እርሻውንም ከኢዮቤልዩ ዓመት ጀምሮ ቢቀድስ፥ እንደ ግምትህ መጠን ይጸናል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እር​ሻ​ው​ንም ከኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመት ጀምሮ ቢሳል፥ እንደ ግምቱ መጠን ይቆ​ማል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እርሻውንም ከኢዮቤልዩ ዓመት ጀምሮ ቢቀድስ፥ እንደ ግምቱ መጠን ይቆማል።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 27:17
7 Referencias Cruzadas  

በዚህም ሁኔታ ኀምሳኛውን ዓመት ለይታችሁ በምድሪቱ ለሚኖሩት ሁሉ ነጻነትን ታውጃላችሁ፤ ከዚያ በፊት የተሸጠ ማናቸውም መሬት ለባለቤቱ ወይም ለዘሩ ይመለሳል፤ ባርያም ሆኖ ለማገልገል የተሸጠ ሰው ወደ ቤተሰቡ ይመለሳል።


በዚህም ዓመት ዘራችሁን አትዘሩም፤ ሳይዘራ ገቦ ሆኖ የበቀለውን እህላችሁን ወይም ካልተገረዘ የወይን ሐረግ ፍሬውን አትሰበስቡም።


“ከዚያ በፊት የተሸጠ መሬት ሁሉ በዚሁ ዓመት ለባለቤቱ ይመለስለታል፤


ሰባተኛው ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን በሚውለው የኃጢአት ስርየት ቀን በመላይቱ ምድር የእምቢልታ ድምፅ የሚያሰማ ሰው ትልካለህ፤


“አንድ ሰው ቤቱን ለእግዚአብሔር የተለየ ስጦታ አድርጎ ሲያቀርብ ካህኑ የቤቱን መልካምነትና መጥፎነት ገምቶ ዋጋውን ይወስን፤ ያም ዋጋ የመጨረሻ ይሆናል።


“አንድ ሰው ከመሬቱ ከፍሎ ለእግዚአብሔር የተለየ ስጦታ አድርጎ ቢያቀርብ፥ ዋጋው መሬቱ በሚቀበለው ዘር መጠን ይወሰን፤ ይኸውም ለእያንዳንዱ ኪሎ ግራም ገብስ ተቀባይ መሬት ኀምሳ ጥሬ ብር ይክፈል።


መሬቱን የሰጠው የኢዮቤልዩ ዓመት ካለፈ ዘግይቶ ከሆነ ግን ካህኑ እስከ ተከታዩ የኢዮቤልዩ ዓመት ያለውን ቀሪ ጊዜ በመገመት ዋጋው እንዲቀነስ ያድርግ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos