Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 18:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ከሌላ ሰው ሚስት ጋር በመተኛት ራስህን ከእርስዋ ጋር አታርክስ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 “ ‘ከባልንጀራህ ሚስት ጋራ ግብረ ሥጋ በመፈጸም፣ ራስህን በርሷ አታርክስ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በእርሷም ራስህን እንዳታረክስ ከባልንጀራህ ሚስት ጋር አትተኛ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ከባ​ል​ን​ጀ​ራህ ሚስት ጋር አት​ተኛ፤ ዘር​ህ​ንም አት​ዝ​ራ​ባት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እንዳትረክስባትም ከባልንጀራህ ሚስት ጋር አትተኛ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 18:20
17 Referencias Cruzadas  

የሐዘንዋም ጊዜ ሲፈጸም ዳዊት ሰው ልኮ ወደ ቤተ መንግሥት አስመጣት፤ ለእርሱም ሚስት ሆና ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ነገር ግን ዳዊት ያደረገው ነገር እግዚአብሔርን አሳዘነ።


“አታመንዝር፤


ቊንጅናዋን አትመኝ፤ በዐይንዋ ጥቅሻ አትማረክ።


ለእስራኤላውያን ጣዖቶች አይሰግድም፤ ወይም በተከለከሉ መስገጃዎች የተሠዋውን ማንኛውንም ነገር አይመገብም፤ የሌላ ሰው ሚስትን አይደፍርም፤ ወይም የወር አበባ ከታያት ሴት ጋር ግንኙነት አያደርግም፤


አንድ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ቢያመነዝር፤ አመንዝራውና አመንዝራይቱ ሁለቱም በሞት ይቀጡ፤


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት መስካሪዎች፥ የቀን ሠራተኞችን ደመወዝ አታለው በሚያስቀሩ አሠሪዎች፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች፥ እናትና አባት የሌላቸው ልጆችንና ስደተኞችን በሚጨቊኑና እኔን በማይፈሩ ሰዎች ላይ ፈጣን ፍርዴን አስተላልፋለሁ።


ባልዋም ሳያውቅ ከሌላ ወንድ ጋር በመተኛት ምንም ሳይታወቅባት ራስዋን አርክሳ ይሆናል፤ እጅ ከፍንጅም ባለመያዝዋ በእርስዋ ላይ መስካሪ አይኖርም፤


አታመንዝሩ ትላለህ፤ አንተ ግን ታመነዝራለህ፤ አንተ ጣዖቶችን ትጸየፋለህ፤ ቤተ መቅደሶቻቸውን ግን ትዘርፋለህ።


ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ ታውቁ የለምን? በዚህ ነገር አትታለሉ፤ ሴሰኞች፥ ወይም ጣዖት አምላኪዎች፥ ወይም አመንዝራዎች፥ ወይም ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ፥


የሥጋ ሥራዎች የታወቁ ናቸው፤ እነርሱም ዝሙት፥ ርኲሰት፥ ስድነት


“አንድ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ ሁለቱም ይገደሉ። በዚህም ዐይነት ይህን ክፉ ነገር ከእስራኤል አስወግዱ።


“አንድ ሰው ለሌላ ሰው የታጨችውን ልጃገረድ ከከተማዋ ውጪ በዋለችበት አግኝቶ በመድፈር ድንግልናዋን ቢገሥ ብቻውን ይገደል።


“ ‘አታመንዝር፤


ጋብቻ በሁሉ ዘንድ የተከበረ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን እግዚአብሔር ስለሚፈርድባቸው ባልና ሚስት ታማኝነትን በማጒደል ጋብቻን አያርክሱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos