Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 17:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ካህኑ ደሙን በድንኳኑ መግቢያ በመሠዊያው ላይ ይርጭ፤ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ጣፋጭ ሽታ ይሆን ዘንድ ስቡንም ያቃጥለው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ካህኑም ደሙን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባለው በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይርጭ፤ ሥቡንም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሽታ እንዲሆን ያቃጥል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ካህኑም በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባለው በጌታ መሠዊያ ላይ ደሙን ይረጨዋል፥ ስቡንም ለጌታ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን ያቃጥለዋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ካህ​ኑም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ባለው በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደሙን ይረ​ጨ​ዋል፤ ስቡ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ያቃ​ጥ​ለ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ካህኑም በመገኛኛው ድንኳን ደጃፍ ባለው በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ደሙን ይረጨዋል፥ ስቡንም ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን ያቃጥለዋል።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 17:6
12 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ የሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ሞራ እንደ መረብ ሆኖ ጉበቱን የሚሸፍነውን ሞራ ሁለቱን ኲላሊቶቹንና እነርሱን የሚሸፍነውን ሞራ ወስደህ በመሠዊያው ላይ አቃጥለው።


ከዚያም በኋላ የአውራውን በግ ሥጋ በሙሉ ለእኔ ለእግዚአብሔር የምግብ መሥዋዕት አድርገህ አቃጥለው፤ ይህም መባ ሽታው እኔን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ሌሎቹ የእስራኤል ሕዝብ እኔን ከድተው ከፊቴ ሲርቁ፥ በቤተ መቅደስ በታማኝነት ጸንተው እኔን ሲያገለግሉ የኖሩና ነገዳቸው ከሌዊ ወገን ሆኖ ከሳዶቅ የተወለዱ ካህናት አሉ፤ ስለዚህም ስብና የመሥዋዕት ደም በማቅረብ በፊቴ ቆመው ሊያገለግሉኝ የሚገባቸው እነርሱ ናቸው፤


“ስለዚህ የእስራኤል ሕዝብ በሜዳ የሚያርዱትን መሥዋዕታቸውን ወደ እግዚአብሔር ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ያመጡታል፤ ካህኑም ለእግዚአብሔር የአንድነት መሥዋዕት አድርጎ ያቀርበዋል።


ካህኑም ይህን ሁሉ ለእግዚአብሔር የምግብ መባ አድርጎ በማቅረብ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።


እጁንም በፍየሉ ራስ ላይ ጭኖ በድንኳኑ ፊት ለፊት ይረደው፤ ካህናቱ ደሙን ተቀብለው በመሠዊያው ዙሪያ ይርጩት፤


ካህኑ ይህን ሁሉ መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ ስብ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለየ ይሁን።


መሥዋዕት አቅራቢው ሰው መባ አድርጎ በሚያቀርበው እንስሳ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ ይረደው፤ የአሮን ዘር የሆኑ ካህናትም ደሙን ተቀብለው በመሠዊያው ዙሪያ ይርጩት።


ይህ የሚቃጠል መሥዋዕት በመሆኑ የአሮን ልጆች በሚቃጠለው መሥዋዕት መሠዊያ ላይ ያቃጥሉት፤ ይህ ዐይነቱ መሥዋዕት መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነው።


እጁን በጠቦቱ ራስ ላይ ጭኖ በድንኳኑ ደጃፍ ፊት ለፊት ይረደው፤ ካህናቱም ደሙን በመሠዊያው ዙሪያ ይርጩት።


ለአንድነት መሥዋዕት የሚቀርቡ እንስሶችን ስብ በመግፈፍ በሚፈጽመው ዐይነት የዚህችንም እንስሳ ስብ ሁሉ ገፎ ያስወግድ፤ መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት አድርጎም በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ በዚህ ዐይነት ካህኑ ስለዚያ ሰው የኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ያቀርባል፤ ያም ሰው ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል።


የላም፥ የበግና የፍየል በኲር ግን መዋጀት የለባቸውም፤ እነርሱ በፍጹም የእኔ ስለ ሆኑ መሥዋዕት ሆነው መቅረብ ይኖርባቸዋል፤ ደማቸውን በመሠዊያው ላይ አፍስሱት፤ ስባቸውንም መዓዛው እኔን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት እንዲሆን በእሳት አቃጥሉት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos