Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘሌዋውያን 13:57 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

57 ሻጋታው እንደገና ቢታይ እርሱ እየተስፋፋ የሚሄድ ስለ ሆነ፥ ባለ ንብረቱ ያቃጥለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

57 ነገር ግን ደዌው በልብሱ ወይም በሸማኔ ዕቃ በተሠራው ወይም በእጅ በተጠለፈው ጨርቅ ላይ ወይም ከቈዳ በተሠራው ዕቃ ላይ ቢታይ፣ መስፋፋቱ ስለ ሆነ ደዌው ያለበት ማንኛውም ነገር በእሳት ይቃጠል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

57 በልብሱም ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከተለፋው ቆዳ በተሠራ በማናቸውም ነገር ላይ ዳግም ቢታይ፥ እየሰፋ የሚሄድ ደዌ ነው፤ ደዌው ያለበትን ነገር በእሳት ታቃጥለዋለህ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

57 በል​ብ​ሱም ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከቆዳ በተ​ደ​ረገ ነገር ላይ ደግሞ ቢታይ፥ የወጣ ለምጽ ነው፤ ደዌው ያለ​በ​ትን ነገር ያቃ​ጥ​ሉት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

57 በልብሱም ወይም በድሩ ወይም በማጉ ወይም ከአጐዛው በተደረገ ነገር ላይ ደግሞ ቢታይ፥ የወጣ ለምጽ ነው፤ ደዌው ያለበትን ነገር አቃጥለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 13:57
10 Referencias Cruzadas  

በጽዮን ያሉ ኃጢአተኞች ይፈራሉ፤ ከሐዲዎችም ይርበደበዳሉ፤ ከእኛ መካከል ከሚባላ እሳትና ከዘለዓለማዊ ነበልባል ጋር ለመኖር የሚችል ማነው ይላሉ።


በድሩም ሆነ በማጉ ላይ፥ እንዲሁም ከሱፍ ወይም ከቈዳ ወይም ከቈዳ በተሠራ ልብስ ላይ ቢታይና፥


ነገር ግን ካህኑ እንደገና በሚመረምርበት ጊዜ ሻጋታው ተቀንሶ ካገኘው፥ የመሻገት ምልክት ያለበትን ስፍራ ብቻ ከጨርቅ ወይም ከቈዳ ልብስ ቀዶ ያውጣው።


ልብሱ በሚታጠብበት ጊዜ የሻጋታው ምልክት ቢጠፋ እንደገና ይጠበው፤ ከዚያም በኋላ የነጻ ይሆናል።”


በዚህ ጊዜ ንጉሡ ተቈጣና ወታደሮቹን ልኮ እነዚያን ገዳዮች አስገደለ፤ ከተማቸውንም በእሳት እንዲያቃጥሉ አደረገ፤


ከዚህ በኋላ በግራው በኩል ያሉትንም እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለተከታዮቹ መላእክት ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ!


እርሱ መንሹ በእጁ ነው። በእርሱም አውድማውን ደኅና አድርጎ ያጠራል። ስንዴውን በጐተራ ይከተዋል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


“ብርቱ ጥንቃቄ በማድረግ ከሥጋ ደዌ በሽታ ተጠበቁ፤ እኔ ባዘዝኳቸው መሠረት ሌዋውያን ካህናት የሚሰጡአችሁን መመሪያ በጥንቃቄ ጠብቁ።


ጸያፍ የሆነ ነገር ከቶ ወደ እርስዋ አይገባም፤ ርኲሰትን የሚያደርግና ውሸት የሚናገር ከቶ ወደ እርስዋ አይገባም፤ ወደ እርስዋ የሚገቡ ስሞቻቸው በበጉ የሕይወት መጽሐፍ የተጻፉ ብቻ ናቸው።


ነገር ግን ፈሪዎች፥ እምነተ ቢሶች፥ ርኩሶች፥ ነፍሰ ገዳዮች፥ አመንዝሮች፥ አስማተኞች፥ ጣዖት አምላኪዎች፥ ውሸታሞች ሁሉ ዕጣ ክፍላቸው በዲን በሚቃጠለው በእሳት ባሕር ውስጥ ይሆናል፤ ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos