Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘሌዋውያን 10:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እግዚአብሔር ባዘዘው የቅባት ዘይት የተቀደሳችሁ ስለ ሆነ ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ውጪ አትውጡ፤ አለበለዚያ ትሞታላችሁ፤” አላቸው፤ እነርሱም ሙሴ እንዳዘዛቸው አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የእግዚአብሔር የመቅቢያ ዘይት በላያችሁ ነውና እንዳትሞቱ ከመገናኛው ድንኳን አትውጡ።” እነርሱም ሙሴ እንዳላቸው አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እንዲሁም የጌታ የቅባት ዘይት በላያችሁ ነውና እንዳትሞቱ ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አትውጡ።” እንደ ሙሴ ቃልም አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቅ​ብ​ዐት ዘይት በላ​ያ​ችሁ ነውና እን​ዳ​ት​ሞቱ ከም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ አት​ውጡ” አላ​ቸው። ሙሴም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው አደ​ረጉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የእግዚአብሔር የቅብዓት ዘይት በላያችሁ ነውና እንዳትሞቱ ከመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አትወጡም አላቸው። እንደ ሙሴ ቃልም አደረጉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘሌዋውያን 10:7
12 Referencias Cruzadas  

የእኔ የአምላኩ የክህነት ቅድስና በእርሱ ላይ ስላለ ከመቅደስ ወጥቶ የአምላኩን መቅደስ አያርክስ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


እኛን ከእናንተ ጋር በክርስቶስ እንድንጸና ያደረገን እግዚአብሔር ነው፤ ለሥራ የለየንም እርሱ ነው፤


ሙሴ ከቅባት ዘይት ጥቂት እና በመሠዊያው ላይ ከነበረውም ከደሙ ጥቂት ወስዶ በአሮንና በልጆቹ እንዲሁም በልብሳቸው ሁሉ ላይ ረጨው፤ በዚህም ሁኔታ ሙሴ እነርሱንና ልብሶቻቸውን ለእግዚአብሔር የተለዩ አደረገ።


እንግዲህ እነዚህን ልብሶች ለወንድምህ ለአሮንና ለልጆቹ አልብሳቸው፤ በክህነት ያገለግሉኝም ዘንድ የወይራ ዘይት በመቀባት የክህነትን ማዕርግ ትሰጣቸዋለህ፤ ትቀድሳቸዋለህም፤


“ደግሞም እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ እንደ ቀባውና ኀይልም እንደ ሰጠው ታውቃላችሁ፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ስለ ነበረ እርሱን መልካም ነገርን እያደረገና በዲያብሎስ የተያዙትን ሁሉ እየፈወሰ ተዘዋወረ።


ኢየሱስም “ሙታንን ተዋቸው፤ ሙታኖቻቸውን ይቅበሩ፤ አንተ ግን ሂድና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት አስተምር!” ሲል መለሰለት።


የቅባቱንም ዘይት በአሮን ራስ ላይ በማፍሰስ ቀብቶ ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ በማድረግ የክህነት ሹመት ሰጠው፤


ከዚህ በኋላ አሮንና ልጆቹ በክህነት ያገለግሉኝ ዘንድ በመቀባት እንዲካኑ አድርግ፤


እግዚአብሔር አሮንን እንዲህ አለው፥


የቅባት ዘይቱንም ወስደህ በራሱ ላይ በማፍሰስ ቀባው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios