Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 5:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 የእግዚአብሔር መልአክ እንዲህ አለ፤ “ሜሮዝን ርገሙ! እዚያ የሚኖሩትን ሁሉ ፈጽማችሁ ርገሙ! እነርሱ በእግዚአብሔር ጐን አልቆሙም፤ ስለ እርሱም ለመዋጋት አልተሰለፉም።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 የእግዚአብሔር መልአክ፣ ‘ሜሮዝን ርገሙ፤’ ‘ሕዝቧንም ዐብራችሁ ርገሙ፤ ከኀያላን ሰልፍ እግዚአብሔርን ለመርዳት፣ በእግዚአብሔርም ጐን ለመቆም አልመጡምና’ አለ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 የጌታ መልአክ፦ ሜሮዝን እርገሙ፥ ጌታን በኃያላን መካከል ለመርዳት፥ ጌታን ለመርዳት አልመጡምና የተቀመጡባትን ሰዎች ፈጽማችሁ እርገሙ አለ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ አለ፥ “ሜሮ​ዝን ርገሙ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርዳታ አል​መ​ጡ​ምና፥ በኀ​ያ​ላን መካ​ከል ወደ እርሱ ርዳታ አል​መ​ጡ​ምና፥ በቤ​ቶ​ችዋ ያሉ​ትን ሰዎች ፈጽ​ማ​ችሁ ርገሙ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 የእግዚአብሔር መልአክ፦ ሜሮዝን እርገሙ፥ እግዚአብሔርን በኃያላን መካከል ለመርዳት፥ እግዚአብሔርን ለመርዳት አልመጡምና የተቀመጡባትን ሰዎች ፈጽማችሁ እርገሙ አለ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 5:23
23 Referencias Cruzadas  

የተቆዓ ከተማ ሰዎች ከዚያ ቀጥሎ ያለውን ክፍል ሠሩ፤ ነገር ግን የከተማይቱ ሹማምንት በተቈጣጣሪዎች የተመደበላቸውን የጒልበት ሥራ መሥራትን እምቢ አሉ።


ዐመፀኞችን ለመቃወም ከጐኔ የሚቆም ማነው? ከክፉ አድራጊዎችስ ጋር ስለ እኔ የሚከራከር ማን ነው?


ቸል በማለት የእግዚአብሔርን ሥራ ከልብ የማይፈጽም ሰው የተረገመ ይሁን! እግዚአብሔር በሚያዘውም ጊዜ ሰይፉን ከደም የሚከለክል የተረገመ ይሁን!


ከዚህ በኋላ በግራው በኩል ያሉትንም እንዲህ ይላቸዋል፤ ‘እናንተ የተረገማችሁ! ከእኔ ወዲያ ራቁ! ለዲያብሎስና ለተከታዮቹ መላእክት ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘለዓለም እሳት ሂዱ!


አሕዛብ ታዛዦች እንዲሆኑ ለማድረግ ክርስቶስ በእኔ ቃልና ሥራ አማካይነት የሠራው ነገር ካልሆነ በቀር ምንም ነገር ለመናገር አልደፍርም።


ጌታን የማይወድ ቢኖር የተረገመ ይሁን! ጌታችን ሆይ፥ ና!


እኛ ለእግዚአብሔር አብረን የምንሠራ አገልጋዮች ነን፤ እናንተም የእግዚአብሔር እርሻና የእግዚአብሔር ሕንጻ ናችሁ።


ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ እንደ መሆናችን የተቀበላችሁትን ጸጋ በከንቱ አታስቀሩት ብለን እንለምናችኋለን።


ለእርስዋም የእግዚአብሔር መልአክ ተገልጦ እንዲህ አላት፤ “አንቺ መኻን ነሽ፤ ልጆችም የሉሽም፤ ነገር ግን ትፀንሺአለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤


የእግዚአብሔር መልአክ ከጌልጌላ ወደ ቦኪም ሄዶ እስራኤላውያንን እንዲህ አላቸው፤ “እኔ ከግብጽ ምድር አውጥቼ ለቀድሞ አባቶቻችሁ ልሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር አመጣኋችሁ፤ እንዲህም አልኩ፦ ‘ከእናንተ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን ከቶ አላፈርስም፤


“በምጽጳ በእግዚአብሔር ፊት ስንሰበሰብ ወደዚያ ያልመጣ ከእስራኤል ነገዶች መካከል አንድ ወገን እንኳ ይገኛልን?” ብለውም ጠየቁ፤ ይህንንም ያሉበት ምክንያት ወደ ምጽጳ ያልሄደ ማንም ሰው ቢገኝ በሞት ለመቅጣት ተማምለው ስለ ነበር ነው።


እነርሱ እንዲህ አሉ፦ “ከእስራኤል ነገዶች መካከል ወደ እግዚአብሔር ወደ ምጽጳ ያልመጣ አለን?” እነሆ ከያቤሽ ገለዓድ ወደ ስብሰባው ማንም አልመጣም ነበር።


የአቢኒዓምን ልጅ ባራቅን የንፍታሌም ድርሻ ከሆነችው ከቃዴስ ከተማ አስጠርታ እንዲህ አለችው፤ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይህን ትእዛዝ ሰጥቶሃል፦ ‘ከንፍታሌምና ከዛብሎን ነገዶች ዐሥር ሺህ ሰዎች መርጠህ ወደ ታቦር ተራራ ውሰዳቸው፤


ከዚህ በኋላ ቀሪዎቹ ወደ መኳንንቱ ወረዱ፤ የእግዚአብሔር ሕዝብ ስለ እኔ ኀያላኑን ለመውጋት ወረዱ።


ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ “ዖፍራ” ተብላ ወደምትጠራው መንደር መጥቶ ከአቢዔዜር ጐሣ የተወለደው የኢዮአስ ንብረት በሆነው የወርካ ዛፍ ሥር ተቀመጠ፤ የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን ምድያማውያን እንዳያዩት ተሸሽጎ በወይን መጭመቂያው ስፍራ የስንዴ ነዶ ይወቃ ነበር።


ወደ ሱኮት በደረሱም ጊዜ ጌዴዎን ለከተማይቱ ሰዎች እንዲህ አለ፤ “እስቲ ለሰዎቼ እንጀራ ስጡልኝ፤ እነርሱ እጅግ ደክመዋል፤ እኔም ዜባሕና ጻልሙናዕ የተባሉትን የምድያማውያን ነገሥታት በማሳደድ ላይ ነኝ።”


የሱኮት መሪዎች ግን “ለአንተ ሠራዊት ምግብ የምንሰጠው በምን ምክንያት ነው? ዜባሕንና ጻልሙናዕን ገና አልማረክህም” አሉት።


ጌዴዎን ወደ ጵኑኤልም ሄዶ በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ያንኑ ጥያቄ አቀረበላቸው፤ ነገር ግን የጵኑኤልም ሰዎች የሱኮት ሰዎች የሰጡትን ተመሳሳይ መልስ ሰጡት።


እዚህ የተሰበሰቡት ሁሉ እግዚአብሔር የሚያድነው በሰይፍና በጦር አለመሆኑን ያውቃሉ፤ ጦርነቱ የእግዚአብሔር ነውና፤ በእናንተም ላይ ድልን እንድንጐናጸፍ ያደርገናል።”


ከዚህ በኋላ ሳኦል ዳዊትን እንዲህ አለው፥ “የእግዚአብሔርን ጦርነት በጀግንነት ብትዋጋ ታላቅዋን ልጄን ሜራብን እድርልሃለሁ፤” ሳኦል ይህን ያለበት ምክንያት በፍልስጥኤማውያን እጅ እንዲሞት እንጂ እርሱ ዳዊትን ለመግደል ስላልፈለገ ነው።


ጌታዬ፥ አንተ የእግዚአብሔርን ጦርነት እየተዋጋህ ነው፤ በምትኖርበትም ዘመን ሁሉ ምንም ዐይነት ክፉ ነገር ማድረግን ስለማትፈልግ ስለ ፈጸምኩት በደል እባክህ ይቅር በለኝ፤ እግዚአብሔር አንተንና ዘሮችህን ለዘለዓለም ያነግሣል፤


ንጉሥ ሆይ! የምልህን አድምጠኝ! አንተን በእኔ ላይ ያነሣሣህ እግዚአብሔር ቢሆን ኖሮ፥ መሥዋዕት በማቅረብ ቊጣውን እንዲመልስ ማድረግ በተቻለ ነበር፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ ሄደህ ባዕዳን አማልክትን አምልክ ብለው እግዚአብሔር ከሰጠኝ ርስት ድርሻ ስላባረሩኝ በእግዚአብሔር ፊት የተረገሙ ይሁኑ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos