Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 4:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሲሣራ በጣም ደክሞት ስለ ነበር ከባድ እንቅልፍ ወሰደው፤ ከዚህ በኋላ የሔቤር ሚስት ያዔል መዶሻና የድንኳን ካስማ ወስዳ በቀስታ ወደ እርሱ ቀረበች፤ ካስማውንም በጆሮ ግንዱ ጠልቆ መሬት እስኪነካ ድረስ ቸነከረችው፤ እርሱም ሞተ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 የሔቤር ሚስት ኢያዔል ግን ሲሣራ ደክሞ፣ ከባድ እንቅልፍም ወስዶት ሳለ፣ የድንኳን ካስማና መዶሻ ይዛ በቀስታ ወደ እርሱ ቀረበች፤ ከዚያም ካስማውን በመዶሻ ጆሮ ግንዱ ላይ መትታ ከመሬት ጋራ ሰፋችው፤ እርሱም ሞተ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 የሔቤር ሚስት ያዔል ግን ሲሣራ ደክሞ፥ ከባድ እንቅልፍም ወስዶት ሳለ፥ የድንኳን ካስማና መዶሻ ይዛ በቀስታ ወደ እርሱ ቀረበች፤ ከዚያም ካስማውን በመዶሻ ጆሮ ግንዱ ላይ መትታ ከመሬት ጋር ሰፋችው፤ እርሱም ሞተ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የሔ​ቤ​ርም ሚስት ኢያ​ዔል የድ​ን​ኳ​ኑን ካስማ ወሰ​ደች፤ በሁ​ለ​ተኛ እጅ​ዋም መዶሻ ያዘች፤ ቀስ ብላም ወደ እርሱ ቀረ​በች፤ በጆሮ ግን​ዱም ካስ​ማ​ውን ቸነ​ከ​ረ​ች​በት፤ እር​ሱም ደክሞ አን​ቀ​ላ​ፍቶ ነበ​ርና ካስ​ማው ወደ መሬት ጠለቀ፤ እር​ሱም ከእ​ግ​ርዋ በታች ተን​ፈ​ራ​ፈረ፤ ተዘ​ር​ሮም ሞተ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የሔቤርም ሚስት ኢያዔል የድንኳን ካስማ ወሰደች፥ በእጅዋም መዶሻ ያዘች፥ ቀስ ብላም ወደ እርሱ ቀረበች፥ በጆሮግንዱ ካስማውን ቸነከረች፥ እርሱም ደክሞ እንቀላፍቶ ነበርና ካስማው ወደ መሬት ጠለቀ፥ እርሱም ሞተ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 4:21
12 Referencias Cruzadas  

ጌታ ሆይ! ተነሥ! አምላኬ ሆይ! መጥተህ አድነኝ! የጠላቶቼን መንጋጋ ስበር፤ ጥርሶቻቸውንም አድቅቅ።


“የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ፤ የሊቃውንትንም ዕውቀት አስወግዳለሁ” ተብሎ ተጽፎአል።


እግዚአብሔር ጥበበኞችን ለማሳፈር በዓለም እንደ ሞኞች የሚቈጠሩትን ሰዎች መረጠ፤ ብርቱዎችንም ለማሳፈር በዓለም እንደ ደካሞች የሚቈጠሩትን መረጠ፤


ከዚህ በኋላ በቅርብ ጊዜ የሞተ የአንድ አህያ መንጋጋ አገኘ፤ ጐንበስ ብሎ አንሥቶም አንድ ሺህ ሰው ገደለበት።


ኤሁድም ሰይፉን ከቀኝ ጭኑ በግራ እጁ መዞ በንጉሡ ሆድ ውስጥ ሻጠ፤


ከዚያም ቀጥሎ የነበረው መሪ የዐናት ልጅ ሻምጋር ነበር፤ እርሱም ስድስት መቶ ፍልስጥኤማውያንን በበሬ ቀንድ በመግደል፥ የእስራኤልን ሕዝብ አዳነ።


ከዚህ በኋላ እርሱ “በድንኳኑ በር ላይ ቁሚ፤ አንድ ሰው መጥቶ ከዚህ ሌላ ሰው እንዳለ ቢጠይቅሽ ማንም የለም በይው” አላት።


ባራቅ ሲሣራን እያሳደደ ሲመጣ ያዔል ልትቀበለው ወጥታ “ወደዚህ ና! አንተ የምትፈልገውን ሰው አሳይሃለሁ” አለችው። ስለዚህም ከእርስዋ ጋር ወደ ውስጥ በገባ ጊዜ የድንኳኑ ካስማ በሲሣራ ጆሮ ግንድ ላይ እንደ ተቸነከረ ሬሳውን በመሬት ላይ ተጋድሞ አየ።


እርስዋም “እሺ፥ እኔም ከአንተ ጋር እሄዳለሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሲሣራን ለሴት አሳልፎ ስለሚሰጥ ድሉ ለአንተ ክብር አይሆንም” አለችው፤ ስለዚህ ዲቦራ ከባራቅ ጋር ወደ ቃዴስ ዘመተች።


ስለዚህም ጎልያድ ዳዊትን “በትር ይዘህ የምትመጣው እኔ ውሻ ነኝን” ካለው በኋላ በአማልክቱ ስም ረገመው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos