Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መሳፍንት 21:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በማግስቱም ጧት በማለዳ ሕዝቡ በዚያ መሠዊያ ሠሩ፤ የሚቃጠልና የደኅንነት መሥዋዕትም አቀረቡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በማግስቱም ጧት ሕዝቡ መሠዊያ ሠሩ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በማግሥቱ ጠዋት ሕዝቡ መሠዊያ ሠሩ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረቡ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በነ​ጋ​ውም ሕዝቡ ማል​ደው ተነሡ፤ በዚ​ያም መሠ​ዊያ ሠሩ፤ የሚ​ቃ​ጠ​ልና የደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም አቀ​ረቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 በነጋውም ሕዝቡ ማልደው ተነሡ፥ በዚያም መሠዊያ ሠሩ፥ የሚቃጠልና የደኅንነት መሥዋዕትንም አቀረቡ።

Ver Capítulo Copiar




መሳፍንት 21:4
13 Referencias Cruzadas  

በዚያው ዕለት ነቢዩ ጋድ ወደ ዳዊት ሄዶ “ወደ ኦርና አውድማ ሄደህ ለእግዚአብሔር መሠዊያውን ሥራ!” አለው፤


ለእግዚአብሔርም መሠዊያ ሠርቶ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕት ሁሉ አቀረበ፤ እግዚአብሔርም የዳዊትን ጸሎት ሰማ፤ በእስራኤል ላይ የወረደውም የቸነፈር መቅሠፍት ከዚህ በኋላ ቆመ።


እንዲሁም በዚያኑ ቀን ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ያለውን አደባባይ መካከለኛ ክፍል ለእግዚአብሔር የተለየ እንዲሆን አደረገ፤ ቀጥሎም በሙሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ የእህል ቊርባንና የኅብረት መሥዋዕት፥ የእንስሶች ስብ ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ ይህንንም ያደረገበት ምክንያት ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ይህን ሁሉ መሥዋዕት መያዝ ስለማይችል ነው።


“መከራ ሲበዛባቸው እኔን ይፈልጋሉ፤ ስለዚህ የሠሩትን በደል ተገንዝበው ወደ እኔ እስከሚመለሱ፥ ድረስ ከእነርሱ እርቃለሁ።”


አምላካችሁ እግዚአብሔር ከነገዶቻችሁ ሁሉ መካከል ለእርሱ መኖሪያ ይሆን ዘንድ በዚያ ስሙ እንዲጠራበት የሚመርጠውን ቦታ ፈልጉና ወደዚያ ሂዱ፤


እኛ መሠዊያ አለን፤ ሆኖም በድንኳኒቱ ውስጥ የሚያገለግሉ ካህናት በዚህ መሠዊያ ላይ ካለው ምግብ ወስደው መብላት አይፈቀድላቸውም።


ከዚህም በኋላ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ወደ ቤትኤል ሄደው አለቀሱ፤ በዚያም ምንም ሳይበሉ እስከ ምሽት በእግዚአብሔር ፊት ተቀምጠው ቈዩ፤ የሚቃጠልና የደኅንነት መሥዋዕት አቀረቡ፤


እነርሱም፦ አቤቱ፥ የእስራኤል አምላክ ሆይ! ዛሬ ከእስራኤል አንድ ነገድ መታጣቱ፥ ስለምን ይህ በእስራኤል ላይ ሆነ? አሉ።


ጌዴዎንም በዚያ መሠዊያ ሠርቶ “እግዚአብሔር የሰላም አምላክ ነው” ብሎ ሰየመው፤ (ይህም መሠዊያ እስከ ዛሬ የአቢዔዜር ጐሣ ይዞታ በሆነችው በዖፍራ ቆሞ ይገኛል።)


በዚያም የፍርስራሽ ጒብታ አናት ላይ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር በደንብ የተስተካከለ መሠዊያ ሥራ፤ ከዚያን በኋላ ሁለተኛውን ኰርማ ውሰድ፤ ሰባብረህ የጣልከውንም የአሼራን ምስል ስብርባሪ በማንደድ ኰርማውን በሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ አቅርብ።”


ከዚያም በራማ ወደሚገኘው መኖሪያ ቤቱ እየተመለሰ እዚያም የዳኝነት ሥራ ይሠራ ነበር፤ በዚህም በራማ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos