Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢያሱ 6:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ኢያሱ ሰላዮች ሆነው የተላኩትን ሁለት ሰዎች “ወደ ጋለሞታይቱ ረዓብ ቤት ሄዳችሁ በገባችሁላት የተስፋ ቃል መሠረት እርስዋንና ቤተሰብዋን አውጡ” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ኢያሱ ምድሪቱን የሰለሉትን ሁለቱን ሰዎች፣ “ወደ ጋለሞታዪቱ ቤት ሂዱ፤ በማላችሁላትም መሠረት እርሷንና የእርሷ የሆነውን ሁሉ ከዚያ አውጡ” አላቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ኢያሱም ምድሪቱን የሰለሉ ሁለቱን ሰዎች እንዲህ አላቸው፦ “ወደ አመንዝራይቱ ቤት ግቡ፥ ከዚያም ሴቲቱንና ያላትን ሁሉ እንደ ማላችሁላት አውጡ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ኢያ​ሱም ምድ​ሪ​ቱን የሰ​ለሉ ሁለ​ቱን ሰዎች፥ “ወደ ዘማ​ዪቱ ቤት ግቡ፤ ከዚ​ያም ሴቲ​ቱ​ንና ያላ​ትን ሁሉ እን​ደ​ማ​ላ​ች​ሁ​ላት አውጡ” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ኢያሱም ምድሪቱን የሰለሉ ሁለቱን ሰዎች፦ ወደ ጋለሞታይቱ ቤት ግቡ፥ ከዚያም ሴቲቱንና ያላትን ሁሉ እንደ ማላችሁላት አውጡ አላቸው።

Ver Capítulo Copiar




ኢያሱ 6:22
13 Referencias Cruzadas  

እንደሚታወቀው ሁሉ የገባዖን ሰዎች እስራኤላውያን አልነበሩም፤ እነርሱ እስራኤላውያን ሊጠብቁአቸው ቃል ስለ ገቡላቸው ከአሞራውያን ተከፍለው ብቻቸውን የሚኖሩ ነበሩ፤ ሳኦል ግን ለእስራኤልና ለይሁዳ ሕዝብ በነበረው ቀኖች ሊያጠፋቸው ዐቅዶ ነበር።


ነገር ግን ዳዊትና ዮናታን እርስ በርሳቸው በገቡት የተቀደሰ ቃል ኪዳን ምክንያት ዳዊት የሳኦልን የልጅ ልጅ የዮናታንን ልጅ መፊቦሼትን አሳልፎ አልሰጣቸውም።


ክፉ ሰዎችን የሚንቅ፥ ለእግዚአብሔር የሚታዘዙትን ግን የሚያከብር፥ ምንም ያኽል ከባድ ቢሆን የገባውን ቃል ኪዳን የሚፈጽም፥


ከንጉሡም ቤተሰብ አንዱን ወስዶ ከእርሱ ጋር የስምምነት ውል አደረገ፤ ለእርሱም ታማኝ እንዲሆንለት በመሐላ ቃል አስገባው፤ ሌሎቹንም የታወቁ ሰዎች ወሰዳቸው።


“ልዑል እግዚአብሔር ሕያው አምላክ እንደ መሆኔ ይህ ንጉሥ በዙፋን ላይ ካስቀመጠው ከባቢሎን ንጉሥ ጋር በመሐላ የገባውን የስምምነት ውል በማፍረሱ ምክንያት በባቢሎን ይሞታል።


አመንዝራይቱ ረዓብ ሰላዮችን በሰላም ስለ ተቀበለቻቸው ከማይታዘዙት ጋር ከመሞት የተረፈችው በእምነት ነው።


“በከተማይቱና በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ ለእግዚአብሔር የተረገመ ሆኖ መደምሰስ አለበት፤ ሴትኛ ዐዳሪዋ ግን የላክናቸውን ሰላዮች ደብቃ ስላዳነች መትረፍ የሚገባቸው እርስዋና ከእርስዋ ጋር በቤትዋ ያሉት ብቻ ናቸው።


እነርሱም ሄደው ረዓብን ከአባትዋና ከእናትዋ ከወንድሞችዋና ከሌሎችም የእርስዋ ወገን ከሆኑት ሰዎች ሁሉ ጋር አውጥተው ከእስራኤላውያን ሰፈር ውጪ አኖሩአቸው።


ስለዚህም ኢያሱ ከእነርሱ ጋር ለሕይወታቸው ዋስትና ቃል ኪዳን በመግባት የሰላም ስምምነት አደረገ። የእስራኤል ሕዝብ መሪዎችም ስምምነቱን ለመጠበቅ ቃል ገቡላቸው።


እርሱም የከተማይቱን መግቢያ አሳያቸው፤ እነርሱም የከተማይቱን ሕዝብ በሰይፍ ፈጁአቸው፤ ያን ሰውና ወገኖቹን ሁሉ ግን በነጻ ለቀቁአቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos