Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዮሐንስ 20:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ይህን ብሎ እፍ አለባቸውና “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ይህን ካለ በኋላም፣ እፍ አለባቸውና እንዲህ አላቸው፤ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ይህንም ብሎ እፍ አለባቸውና “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ይህ​ንም ብሎ እፍ አለ​ባ​ቸው፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተቀ​በሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ይህንም ብሎ እፍ አለባቸውና፦ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ።

Ver Capítulo Copiar




ዮሐንስ 20:22
17 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር አምላክ ከመሬት ዐፈር ወስዶ፥ ሰውን ከዐፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም ሕይወትን የሚሰጥ እስትንፋስ “እፍ” አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ፍጡር ሆነ።


የፈጠረኝ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው፤ ሕይወትም የሰጠኝ ሁሉን የሚችል አምላክ እስትንፋስ ነው።


እግዚአብሔር ሰማያትን በቃሉ፥ በሰማይ የሚገኙትን ፍጥረቶች በትእዛዙ ፈጠረ።


እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! ለነፋስ ትንቢት ተናገር፤ ነፋስ ከአራቱም ማእዘን መጥቶ ሕይወት እንዲያገኙ በእነዚህ በድኖች ላይ እንዲነፍስ ንገረው።”


እኔ አብን እለምነዋለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ከእናንተ ጋር የሚኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል።


“ነገር ግን ከአብ የሚወጣና እኔም ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኙ የእውነት መንፈስ ሲመጣ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል።


እኔ ግን እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ የእኔ መሄድ ለእናንተ ይጠቅማችኋል፤ እኔ ካልሄድኩ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣም፤ እኔ ከሄድኩ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ እንደገና “ሰላም ለእናንተ ይሁን! አብ እኔን እንደ ላከኝ እኔም እናንተን እልካችኋለሁ” አላቸው።


እናንተ የሰዎችን ኃጢአት ይቅር ብትሉ ይቅር ይባልላቸዋል፤ እናንተ የሰዎችን ኃጢአት ይቅር ባትሉ ግን፥ ይቅር አይባልላቸውም” አላቸው።


ይህንንም የተናገረው በእርሱ የሚያምኑ ስለሚቀበሉት ስለ መንፈስ ቅዱስ ነበር፤ ኢየሱስ ገና ወደ ክብር ስላልወጣ መንፈስ ቅዱስ ገና አልተሰጠም ነበር።


“እነዚህ ሰዎች እንደ እኛ መንፈስ ቅዱስን ተቀብለዋል፤ ታዲያ፥ እነርሱ በውሃ እንዳይጠመቁ ማን ይከለክላቸዋል?” ሲል ተናገረ።


“ባመናችሁ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀብላችሁ ነበርን?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም “አልተቀበልንም፤ መንፈስ ቅዱስ መኖሩን እንኳ ሰምተን አናውቅም” ሲሉ መለሱለት።


ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፤ “ንስሓ ግቡ፤ ኃጢአታችሁም ይቅር እንዲባልላችሁ እያንዳንዳችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠመቁ፤ የእግዚአብሔር ስጦታ የሆነውን መንፈስ ቅዱስንም ትቀበላላችሁ፤


ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፤ መንፈስ ቅዱስ እንዲናገሩ በሰጣቸው ችሎታ መጠን በሌሎች ቋንቋዎች መናገር ጀመሩ።


በዚህ ጊዜ ጴጥሮስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “እናንተ የሕዝብ አለቆችና ሽማግሌዎች ሆይ!


ስለዚህ የሰማርያ ሰዎች መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ጴጥሮስና ዮሐንስ ሄደው ጸለዩላቸው።


ማወቅ የምፈልገው ይህን ብቻ ነው፤ ለመሆኑ እናንተ መንፈስ ቅዱስን የተቀበላችሁት ሕግን በመፈጸም ነውን? ወይስ የምሥራቹን ቃል ሰምታችሁ በማመን ነው?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos