Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 20:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ምንም እንኳ ሀብታም ቢሆን ብስጭት ይደርስበታል፤ ብዙ ችግርም ያጋጥመዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 በተድላ መካከል እያለ ጕስቍልና ይመጣበታል፤ በከባድ መከራም ይዋጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በጠገበ ጊዜ ይጨነቃል፥ የጉስቁልናም ሁሉ እጅ ታገኘዋለች።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በጠ​ገበ ጊዜ ይጨ​ነ​ቃል፤ መከ​ራም ሁሉ ያገ​ኘ​ዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 በጠገበ ጊዜ ይጨነቃል፥ የችግረኞችም ሁሉ እጅ ታገኘዋለች።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 20:22
13 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ባገልጋዮቹ በነቢያት አማካይነት ይሁዳን ስለ ማጥፋት የተናገረው ትንቢት እንዲፈጸም ወራሪ ቡድኖች ባቢሎናውያንን፥ ሶርያውያንን፥ ሞአባውያንንና ዐሞናውያንን በኢዮአቄም ላይ አስነሣበት።


የሳባ ሰዎች መጥተው አደጋ በመጣል ሁሉንም ዘርፈው ወሰዱ፤ አገልጋዮችህን ሁሉ በሰይፍ ገደሉአቸው፤ እኔ ብቻ አምልጬ የሆነውን ነገር ልነግርህ መጣሁ።”


ይኸኛው መልእክተኛ ተናግሮ ሳይጨርስ ሌላ መልእክተኛ መጥቶ፥ “በሦስት ቡድን የተከፈሉ የከለዳውያን ዘራፊዎች በድንገት አደጋ ጣሉብን፤ ግመሎቹን በሙሉ ወሰዱአቸው፤ አገልጋዮችህንም በሙሉ በሰይፍ ገደሉአቸው፤ እኔ ብቻ አምልጬ የሆነውን ነገር ልነግርህ መጣሁ” አለው።


ባለጸጋ አይሆንም፥ ሀብቱም ለብዙ ጊዜ አይቈይም፤ በምድር ላይም አይስፋፋም።


እግዚአብሔር ለክፉ ሰዎች አሳልፎ ሰጠኝ፤ በዐመፀኞች እጅ ላይ ጣለኝ።


የብርቱ ዕርምጃው ርዝመት እያጠረ ይሄዳል፤ የራሱም የተንኰል ዕቅድ ይጥለዋል።


በልቼ እጠግባለሁ ሲል እግዚአብሔር ኀይለኛ ቊጣውን ያወርድበታል። መዓቱንም በእርሱ ላይ ያዘንብበታል።


በዚያ ክፉዎች አስቸጋሪነታቸው ይቀራል፤ በአድካሚ ሥራም የኖሩ ያርፋሉ።


ሰብሉንም የተራቡ ሰዎች ይበሉታል፤ በእሾኽ መካከል የበቀለውን እንኳ አይተውለትም፤ የተጠሙ ሰዎችም ሀብቱን ለመውሰድ ይጐመዣሉ።


የዘመኔን መለኪያ ከእጅ መዳፍ እንዳይበልጥ አድርገህ አሳጠርከው፤ ዕድሜዬም በአንተ ፊት ከምንም አይቈጠርም፤ በእርግጥ የሰው ሕይወት እንደ ነፋስ ሽውታ ነው።


ሀብታቸውን ዘርፈውና መዝብረው ሕዝቡን እንደ መንገድ ላይ ጭቃ እንዲረግጡ በከሐዲውና ቊጣዬንም ባነሣሣው ሕዝብ ላይ አሦራውያንን አስነሥቼ እልካቸዋለሁ።”


እርስዋ ለራስዋ ክብርንና ምቾትን የሰጠችውን ያኽል ሥቃይና ሐዘን ስጡአት፤ እርስዋ በልብዋ ‘እንደ ንግሥት ተቀምጬአለሁ፤ መበለትም አይደለሁም፤ ሐዘንም ከቶ አይደርስብኝም’ በማለት ትመካለች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios