Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢዮብ 10:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ኃጢአት ብሠራ ወዲያው ችግር ውስጥ እወድቃለሁ ደግ ነገር ብሠራም አልመሰገንም ተጐሣቊዬ ኀፍረት ደርሶብኛል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 በደለኛ ብሆን ወዮልኝ፤ ንጹሕ ብሆንም፣ ራሴን ቀና አላደርግም፤ ውርደትን ተከናንቤአለሁና፤ በመከራም ተዘፍቄአለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 በደለኛ ብሆን ወዮልኝ፥ ጻድቅም ብሆን ራሴን አላነሣም፥ ጉስቁልናን ተሞልቻለሁና፥ መከራዬንም ተመልክቻለሁና።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በደ​ለኛ ብሆን ወዮ​ልኝ፤ ጻድ​ቅም ብሆን ራሴን አላ​ነ​ሣም፤ ጕስ​ቍ​ል​ና​ንም ጠገ​ብ​ኋት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በደለኛ ብሆን ወዮልኝ፥ ጻድቅም ብሆን ራሴን አላነሣም፥ ጕስቍልናን ተሞልቻለሁ፥ መከራዬንም ተመልክቻለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 10:15
23 Referencias Cruzadas  

በደለኛ አለመሆኔንና ከአንተም እጅ ማንም ሊያድነኝ እንደማይችል አንተ ታውቃለህ።


እኔ እንኳ ሳስበው ያስደነግጠኛል፤ ሰውነቴንም በፍርሃት ያንቀጠቅጠዋል።


ስለዚህ በእርሱ ፊት መቆም እጅግ ያስፈራኛል፤ ይህን ባሰብኩ ጊዜ እንኳ ፈራሁ።


“ጠላቶቼ እንደ ኃጢአተኞች፥ ተቃዋሚዎቼም እንደ ግፈኞች ይፈረድባቸው።


በደል እንዳይሆንባችሁ ተመለሱ፤ አሁንም ተመለሱ፤ እኔ ትክክለኛ ነኝ።


የፈለገውን ቢወስድ ማንም አይከለክለውም፤ ‘ለምን እንዲህ ታደርጋለህ?’ ብሎ ሊጠይቀው የሚደፍርም የለም።


ንጹሕ ሆኜ ብገኝ እንኳ፥ ፈራጁ አምላክ እንዲምረኝ እለምነዋለሁ እንጂ መልስ ልሰጠው አልደፍርም።


እንግዲህ በደለኛ ሆኜ ከተቈጠርኩ፥ በከንቱ መድከሜ ለምንድን ነው?


እኔ ሕግህን አልረሳሁም፤ ስለዚህ ችግሬን ተመልክተህ አድነኝ።


ችግሬንና ሥቃዬን ተመልከት፤ ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር በልልኝ።


እንዲህም የሆንኩት ጠላቶቼ በሚበቀሉኝ ጊዜ ሌሎች ሰዎች ሲያፌዙብኝና ሲሳለቁብኝ በመስማቴ ነው።


እግዚአብሔር ሆይ! አንተን ይሹ ዘንድ ፊታቸውን በኀፍረት ሸፍን፤


ክፉዎች ወደ ሙታን ዓለም ይወርዳሉ። እግዚአብሔርንም ከረሱ ሕዝቦች ጋር ይቀላቀላሉ።


ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “በግብጽ ያለውን የሕዝቤን ጭንቀት አይቻለሁ፤ በአስጨናቂዎቻቸው ምክንያት የሚጮኹትን ጩኸት ሰምቼአለሁ፤ ጭንቀታቸውንም ዐውቃለሁ።


ምንም ነገር ስለማይሳካላቸውና የክፉ ተግባራቸውን ዋጋ ስለሚያገኙ ለክፉዎች ወዮላቸው!


እኔም “እነሆ አንደበቶቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል የምኖር፥ አንደበቴም የረከሰብኝ ሰው ነኝ፤ ንጉሡን የሠራዊት አምላክን በዐይኖቼ አይቼአለሁና መጥፋቴ ስለ ሆነ ወዮልኝ!” አልኩ።


“እግዚአብሔር ሆይ! ራሴ እንዴት እንደ ተበጠበጠ ተመልከት! በአንተ ላይ ስላመፅሁ ሆዴ ተሸበረ፤ ልቤም ተሰበረ፤ በመንገድም ሆነ በቤት ውስጥ ሕዝቤ እያለቀ ነው።


በዚያን ጊዜ በጻድቅና በኃጢአተኛ ለእግዚአብሔር በሚታዘዝና በማይታዘዝ ሰው መካከል ያለውን ልዩነት እንደገና ታያላችሁ።”


እናንተም እንዲሁ የታዘዛችሁትን ሁሉ በፈጸማችሁ ጊዜ፥ ‘የማንጠቅም አገልጋዮች ነን፤ የፈጸምነውም ግዳጃችንን ብቻ ነው’ በሉ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios