ኤርምያስ 52:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ድስቶችን መሠዊያውን የሚያጸዱበትን የአካፋ ቅርጽ ያለውን መጫሪያውንና የዐመድ ማጠራቀሚያዎቹን ጐድጓዳ ሳሕኖችን፥ ጭልፋዎችንና ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት ከነሐስ የተሠሩ ሌሎችንም ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ ወሰዱ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ከእነዚህም ሌላ ምንቸቶቹን፣ መጫሪያዎቹን፣ መኰስተሪያዎቹን፣ ወጭቶቹን፣ ጭልፋዎቹንና ለቤተ መቅደስ አገልግሎት የሚውሉትን የናስ ዕቃዎች በሙሉ ወሰዱ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 የሸክላ ድስቶችንና መጫሪያዎችንም፥ መኰስተሪያዎችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችንም፥ ሙዳዮችና የሚገለገሉባቸውንም የናስ ዕቃዎች ሁሉ ወሰዱ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 ምንቸቶቹንና መጫሪያዎችን፥ መኰስተሪያዎችንና ድስቶችን፥ ጭልፋዎችንም፥ የሚያገለግሉበትንም የናስ ዕቃ ሁሉ ወሰዱ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 ምንቸቶቹንና መጫሪያዎችንም መኰስተሪያዎችንና ድስቶችን ጭልፋዎችንም የሚያገለግሉበትንም የናስ ዕቃ ሁሉ ወሰዱ። Ver Capítulo |
ሑራም በተጨማሪ ምንቸቶችን፥ መጫሪያዎችንና ማንቈርቈሪያዎችንም ሠራ፤ በዚህ ሁኔታም ሑራም ለንጉሥ ሰሎሞን እንዲሠራለት ቃል በገባለት መሠረት ለቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚውለውን ዕቃ ሁሉ ሠርቶ ፈጸመ፤ የሠራቸውም ዕቃዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፦ ሁለት ምሰሶዎች፥ በምሰሶዎቹ ጫፍ ላይ የሚገኙት የሳሕን ቅርጽ ያላቸው ሁለት ጒልላቶች፥ ሁለቱን ጉልላቶች ለማስጌጥ በእያንዳንዱ ጒልላት ላይ የሚገኙት በመርበብ አምሳል የተቀረጹት ሁለት ሰንሰለቶች፥ ጉልላቶቹን ለማስጌጥ በእያንዳንዱ ጒልላት ላይ በሁለት ዙር የተቀረጹ ከነሐስ የተሠሩ አራት መቶ የሮማን ፍሬ ምስሎች፥ ዐሥሩ ባለመንኰራኲር የዕቃ ማስቀመጫዎች፥ ዐሥሩ የመታጠቢያ ገንዳዎች፥ ትልቁ ገንዳ፥ በርሜሉን ደግፈው የያዙት የዐሥራ ሁለቱ በሬዎች ቅርጾች፥ ምንቸቶች፥ መጫሪያዎች፥ ሜንጦዎችና ሌሎችም እነዚህን የመሳሰሉ ዕቃዎች በእጅ ጥበብ ሠራ። ታዋቂ የሆነው ሑራም በንጉሥ ሰሎሞን ትእዛዝ መሠረት ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ይውሉ ዘንድ እነዚህን ዕቃዎች ሁሉ የሠራው ከተወለወለ ነሐስ ነበር።