ኤርምያስ 42:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 እኔም “መልካም ነው፤ ልክ እናንተ በጠየቃችሁት መሠረት ወደ እግዚአብሔር አምላካችሁ እጸልይላችኋለሁ፤ የሚገልጥልኝንም ሁሉ ከእናንተ ምንም ነገር ሳልሰውር እነግራችኋለሁ” ብዬ መለስኩላቸው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ነቢዩ ኤርምያስም፣ “ሰምቻችኋለሁ፤ እንዳላችሁት ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር በርግጥ እጸልያለሁ፤ እግዚአብሔር ያለኝን ሁሉ አንዳች ሳላስቀር እነግራችኋለሁ” አላቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ነቢዩም ኤርምያስ እንዲህ አላቸው፦ “ሰምቻችኋለሁ፤ እነሆ፥ እንደ ቃላችሁ ወደ ጌታ ወደ አምላካችሁ እጸልያለሁ፤ ጌታም የሚመልስላችሁን ቃል ሁሉ እነግራችኋለሁ፥ ከእናንተም ምንም አልሸሽግም።” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ነቢዩ ኤርምያስም አላቸው፥ “ሰምታችኋል፤ እነሆ እንደ ቃላችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ እግዚአብሔርም የሚመልስልኝን ሁሉ እነግራችኋለሁ፤ ከእናንተም አንድም ቃል አልሸሽግም።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ነቢዩም ኤርምያስ፦ ሰምቻችኋለሁ፥ እነሆ፥ እንደ ቃላችሁ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፥ እግዚአብሔርም የሚመልስላችሁን ሁሉ እነግራችኋለሁ፥ ከእናንተም ምንም አልሸሽግም አላቸው። Ver Capítulo |