Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 36:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ነገር ግን በሚቀጥለው ጊዜ ሕዝቡ በመጾም ላይ ሳሉ አንተ ወደዚያ እንድትሄድ እፈልጋለሁ፤ እግዚአብሔር ለእኔ የነገረኝን ቃል ሁሉ አንድ በአንድ እየነገርኩህ በሚጠቀለል ብራና ላይ የጻፍከውን ሁሉ ድምፅህን ከፍ አድርገህ አንብብላቸው፤ ከገጠር ከተሞቻቸው የመጡ የይሁዳ ሕዝብ ጭምር ሁሉም በሚሰሙበት ቦታ ይህን አድርግ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሄደህ፣ በቃል እየነገርሁህ በብራናው ላይ የጻፍኸውን የእግዚአብሔርን ቃል በጾም ቀን ለተሰበሰበው ሕዝብ አንብብ፤ ከየከተሞቻቸው ለመጡት ለይሁዳ ሕዝብ ሁሉ አንብብ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 አንተ ግን ሂድ፥ እየነገርሁህም የጻፍኸውን የጌታን ቃላት በጾም ቀን በጌታ ቤት በሕዝቡ ጆሮ ከክርታሱ አንብብ፤ እንዲሁም ደግሞ ከከተሞቻቸው በሚወጡ በይሁዳ ሰዎች ሁሉ ጆሮ አንብበው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 አንተ ግን ገብ​ተህ ከአፌ የጻ​ፍ​ኸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በጾም ቀን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሕ​ዝቡ ጆሮ በክ​ር​ታሱ አን​ብብ፤ ደግ​ሞም ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው በሚ​ወጡ በይ​ሁዳ ሰዎች ሁሉ ጆሮ አን​ብ​በው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 አንተ ግን ሂድ፥ ከአፌም የጻፍኸውን የእግዚአብሔርን ቃል በጾም ቀን በእግዚአብሔር ቤት በሕዝቡ ጆር በክርታሱ አንብብ፥ ደግሞም ከከተሞቻቸው በሚወጡ በይሁዳ ሰዎች ሁሉ ጆሮ አንብበው።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 36:6
13 Referencias Cruzadas  

ስለዚህም እኔ እነርሱን ለመቅጣት በእነርሱ ላይ ክፉ ነገር የማደርግ መሆኔን ለይሁዳና ለኢየሩሳሌም ሕዝብ ንገራቸው፤ ኃጢአት መሥራትን እንዲተዉና አካሄዳቸውንና አሠራራቸውን ሁሉ እንዲለውጡ ምከራቸው።


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ቃሉን እንድናገርበት ካዘዘኝ ከቶፌት ተመልሼ መጣሁ፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባይም ቆሜ እንዲህ ብዬ ነገርኳቸው፤


“እኔ እግዚአብሔር አንተን ማናገር ከጀመርኩበት ማለትም ኢዮስያስ ከነገሠበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ስለ እስራኤል፥ ስለ ይሁዳ ሕዝብና ስለ ሌሎችም ሕዝቦች ሁሉ የነገርኩህን ቃል ሁሉ በብራና ጻፈው፤


ስለዚህም የኔሪያን ልጅ ባሮክን ጠርቼ እግዚአብሔር የነገረኝን ቃል ሁሉ አንድ በአንድ እየነገርኩት በሚጠቀለል ብራና ጻፈው፤


“በአራተኛው፥ በአምስተኛው፥ በሰባተኛውና በዐሥረኛው ወር ትጠብቁት የነበረው ጾም ሁሉ ለይሁዳ ሕዝብ የተድላና የደስታ በዓል ይሆንላቸዋል፤ እናንተ ግን እውነትንና ሰላምን ውደዱ።”


በጒዞአችን ላይ ብዙ ጊዜ በመባከኑና የጾም ጊዜ በማለፉ ምክንያት በዚህ ጊዜ በባሕር ላይ መጓዝ አደገኛ ስለ ነበር ጳውሎስ ለሰዎቹ እንዲህ ሲል አስጠነቀቃቸው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos