Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 30:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ነገር ግን እናንተን ግጠው የበሉአችሁ ሁሉ እነርሱም በፈንታቸው ተግጠው ይበላሉ፤ ጠላቶቻችሁ ሁሉ ተማርከው ይወሰዳሉ፤ ሲዘርፉአችሁ የነበሩት ሁሉ ይዘረፋሉ። የቀሙአችሁ ሁሉ እነርሱም በተራቸው እንዲቀሙ አደርጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 “ ‘ነገር ግን አሟጥጠው የበሉህ ሁሉ እንደዚያው ይበላሉ፤ ጠላቶችህ ሁሉ ለምርኮ ዐልፈው ይሰጣሉ፤ የሚዘርፉህ ይዘረፋሉ፤ የሚበዘብዙህም ሁሉ ይበዘበዛሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ስለዚህ የሚውጡህ ሁሉ ይዋጣሉ፥ ጠላቶችህም ሁሉ አንድም ሳይቀሩ ይማረካሉ፤ የዘረፉህም ይዘረፋሉ፥ የበዘበዙህንም ሁሉ ለመበዝበዝ አሳልፌ እሰጣለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ስለ​ዚህ የሚ​በ​ሉህ ሁሉ ይበ​ላሉ፤ የሚ​ማ​ር​ኩ​ህም ሁላ​ቸው ይማ​ረ​ካሉ፤ የዘ​ረ​ፉ​ህም ይዘ​ረ​ፋሉ፤ የሚ​ማ​ር​ኩ​ህ​ንም ሁሉ ለመ​ማ​ረክ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ስለዚህ የሚውጡህ ሁሉ ይዋጣሉ፥ ጠላቶችህም ሁላቸው ይማረካሉ፥ የዘረፉህም ይዘረፋሉ፥ የበዘበዙህንም ሁሉ ለመበዝበዝ አሳልፌ እሰጣለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 30:16
44 Referencias Cruzadas  

ቊጣህን አንተን በማያውቁና ስምህን በማይጠሩ ሕዝቦች ላይ አፍስሰው፤ እነርሱ ሕዝብህን ፈጅተዋል፤ ሁላችንንም ፈጽመው በመደምሰስ፥ አገራችንን አውድመዋል።


አንተ ማንም ጥፋት ሳያደርስብህ ጥፋተኛ የሆንክ! ማንም ሳይከዳህ ከዳተኛ የሆንክ ወዮልህ! ጥፋትን ማድረስህን ስታቆም ትጠፋለህ፤ ከዳተኛነትህንም ስታቆም ክዳት ይደርስብሃል።


ለእርሱ ብትታዘዝና እኔ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብትፈጽም ጠላቶችህን እጠላለሁ፤ ተቃዋሚዎችህንም እዋጋለሁ፤


እናንተን የሚነካ የእርሱን ዓይን ብሌን እንደሚነካ ሆኖ ይቈጠራል። የክብር ጌታ በበዘበዙአችሁ ሕዝቦች ላይ በላከኝ ጊዜ የተናገራቸው ቃላት እነዚህ ናቸው።


“ለመማረክ የተመደበ ይማረካል፤ በሰይፍ ለመገደል የተመደበ በሰይፍ ይገደላል፤” እንግዲህ የቅዱሳን ትዕግሥትና እምነት የሚያስፈልገው በዚህ ጊዜ ነው።


“ኢየሩሳሌምን በዙሪያዋ ላሉ ሕዝቦች ጠጥተውት እንደሚያንገዳግድ የወይን ጠጅ ዋንጫ አደርጋታለሁ፤ እነርሱ ኢየሩሳሌምን በሚይዙ ጊዜ የቀሩትም የይሁዳ ከተሞች ይከበባሉ።


የእናንተንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ለይሁዳ ሕዝብ ተላልፈው እንዲሸጡ አደርጋለሁ፤ እነርሱም ሩቅ ላሉት ለሳባውያን ይሸጡአቸዋል፤ ይህንንም የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


የብዙ አሕዛብ መንግሥታት የእስራኤል ሕዝብ እግዚአብሔር ወደ ሰጣቸው አገር እንዲመለሱ ይረዱአቸዋል፤ አሕዛብ እንደ ባሪያዎች ሆነው የእስራኤልን ሕዝብ ያገለግላሉ፤ ቀድሞ እስራኤልን ማርከው የነበሩ አሁን ደግሞ በእስራኤል እጅ ይማረካሉ፤ ስለዚህም የእስራኤል ሕዝብ ቀድሞ ይጨቊኑአቸው የነበሩትን ሁሉ የመግዛት ሥልጣን ይኖራቸዋል።


ጽዮንን የሚጠላ ሁሉ ይሸነፍ! ወደ ኋላውም ይመለስ!


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በሕዝቤ ላይ የደረሰውን የሞአብን ሕዝብ ፌዝና የአሞንን ሕዝብ ስድብ ሰምቼአለሁ፤ እነርሱም እንዴት አድርገው እንዳፌዙባቸውና ርስታቸውንም ለመውሰድ እንደ ዛቱባቸው ዐውቄአለሁ።


አንተ ራስህ ጠጥተህ በመስከር ትንገዳገዳለህ፤ አንተም በተራህ በክብር ፈንታ ውርደትን ትለብሳለህ፤ እግዚአብሔር ኀይለኛ የቅጣት ጽዋ እንድትጠጣ ያደርግሃል፤ ክብርህን ወደ ውርደት ይለውጣል።


ተቃዋሚዎቹን በኀይለኛ ጐርፍ ያጥለቀልቃቸዋል፤ ጠላቶቹንም ወደ ጨለማ ያሳድዳቸዋል።


ጠላቴም ይህን ሁሉ ያያል፤ “አምላክህ እግዚአብሔር የት አለ?” ይለኝ የነበረው ጠላቴ ኀፍረትን ይከናነባል፤ እኔ የጠላቴን ውድቀት አያለሁ፤ በመንገድ ዳር እንዳለ ጭቃ ሲረገጥም እመለከታለሁ።


አሁን ግን ብዙ ሕዝቦች በእናንተ ላይ ተሰብስበው እንዲህ ይላሉ፦ “ኢየሩሳሌም ትርከስ! እኛም መፍረስዋን እንይ!”


“ ‘ለብዙ ጊዜ ከቈየው ጥላቻችሁ የተነሣ በኃጢአቱ ምክንያት በደረሰበት የመጨረሻ ቅጣትና በመከራው ጊዜ የእስራኤልን ሕዝብ ለሰይፍ አሳልፋችሁ ሰጣችሁ።


እናንተ ለእስራኤላውያን እንደ ሸምበቆ በትር ደካሞች ስለ ሆናችሁ በዚያን ጊዜ እናንተ የግብጽ ሕዝብ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።


“ጠላቶቼ ሁሉ ማንም የሚያጽናናኝ ሰው በሌለበት እንዴት እንደምቃትትና እንደምቸገር ሰሙ፤ አንተ ያደረግኸው መሆኑንም ዐውቀው ተደሰቱ፤ በእነርሱ ላይ ልታመጣባቸው የወሰንከውን ቀን አምጣና እንደ እኔ ይሁኑ።


እስራኤል ሆይ! አንቺ እንደ መከር መጀመሪያ ፍሬ ለእኔ የተለየሽ ነበርሽ፤ ለእኔም የተቀደስሽ ርስት ሆነሽ ነበር፤ ስለዚህም አንቺን መጒዳት በሚፈልጉት ሁሉ ላይ መከራና መቅሠፍት አመጣሁባቸው።’ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


አንቺን ለማጥፋት የሚሠራ መሣሪያ ዘላቂነት አይኖረውም፤ ለሚከሱሽ ሁሉ በቂ መልስ ይኖርሻል፤ የእኔ አገልጋዮች ርስትና ከእኔ የሚፈረድላቸው ፍርድ ይህ ነው፤” ይላል እግዚአብሔር።


በአንቺ ላይ አደጋ ለማድረስ የተነሡ ቢኖሩ ከእኔ የተላኩ ስላልሆኑ ይወድቃሉ።


ኢየሩሳሌምን እንዲወጉ እግዚአብሔር ሕዝቦችን ሰብስቦ ይመጣል፤ ከተማይቱ ትያዛለች፤ ቤቶች ይበዘበዛሉ፤ ሴቶች ይደፈራሉ፤ ከሕዝቡም እኩሌታው ተማርኮ ይሄዳል፤ የቀሩት ግን ከከተማይቱ አይወጡም።


ስለዚህም መልአኩ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሚለውን ቃል እንዲህ ብለህ ዐውጅ አለኝ፥ “እኔ ለተቀደሰችው ከተማዬ ለኢየሩሳሌም ታላቅ ፍቅርና ብርቱ ቅናት አለኝ፤


“የባቢሎን ምርኮኞችና በባቢሎን የነበሩ ስደተኞች ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። አምላካችን እግዚአብሔር በባቢሎናውያን ላይ ስለሚበቀለው በቀል የሚናገሩትን አድምጡ።”


ከዚህም በኋላ ሰባው ዓመት ሲፈጸም ባቢሎንን፥ ሕዝብዋንና ንጉሥዋን በበደላቸው ምክንያት እቀጣቸዋለሁ፤ የባቢሎንም ምድር ለዘለዓለም ባድማ ሆና እንድትቀር አደርጋለሁ፤


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ለሕዝቤ ለእስራኤል የሰጠኋቸውን ምድር ስላጠፉት ስለ እስራኤል ጐረቤቶችም የምናገረው ነገር አለኝ፤ እነዚያን ክፉ ሕዝቦች ከየአገራቸው ነቃቅዬ እወስዳቸዋለሁ፤ የይሁዳንም ሕዝብ ከመካከላቸው መንጥቄ አወጣቸዋለሁ።


ጠላቶቻችን እስከ ዳን ከተማ ደርሰዋል፤ ፈረሶቻቸው ሲያንኮራፉ ድምፃቸው ይሰማል፤ ሰንጋ ፈረሶቻቸውም ሲያሽካኩ ምድር ትናወጣለች፤ ጠላቶቻችን የመጡት ምንም ሳያስቀሩ ሕዝባችንንና ከተሞቻችንን እንዲሁም በውስጡ ያለውን ነገር ሁሉ ለማጥፋት ነው።”


ኃጢአታችሁ የበዛ ክፋታችሁም እጅግ ከፍ ያለ በመሆኑ ፈውስ ስለማይገኝላችሁ፥ ስለ ቊስላችሁ ሕመም አታጒረምርሙ፤ እኔ እንዲህ አድርጌ እቀጣችኋለሁ።


እነዚህንም መርገሞች ሁሉ አንተን በሚጠሉህና በሚጨቊኑህ ጠላቶችህ ላይ ይመልስባቸዋል፤


እስራኤላውያንም እነርሱን አሳደው ከተመለሱ በኋላ ፍልስጥኤማውያን የነበሩበትን ሰፈር ዘረፉ።


ይኸውም እግዚአብሔር ስለሚከራከርላቸውና የሚያስጨንቁአቸውንም ስለሚያስጨንቅ ነው።


“ ክፉ ሥራቸውን ሁሉ ተመልከት፤ በበደሎቼ ሁሉ ምክንያት በእኔ ላይ እንዳደረግኸው በእነርሱም ላይ አድርግ ዘወትር ስለምቃትት ልቤ እየደከመብኝ ነው።”


ሰላም አግኝተው በጸጥታ በሚኖሩ በአሕዛብ መንግሥታት ላይ እጅግ ተቈጥቼአለሁ፤ ምክንያቱም እኔ ሕዝቤን ከመቅጣት መለስ ባልኩበት ጊዜ እነዚያ የአሕዛብ መንግሥታት ሕዝቤን ከተጠበቀው በላይ አሠቃይተዋል።


በተቀደሰችው ምድር ይሁዳን የራሱ ርስት ያደርጋታል፤ ኢየሩሳሌምንም እንደገና ይመርጣታል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios