Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 58:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እናንተ በምትጾሙበት ጊዜ ሰውነታችሁን ታጐሳቊላላችሁ፤ ራሳችሁን እንደ ሸምበቆ ዝቅ ታደርጋላችሁ፤ አመድ ነስንሳችሁ፥ ማቅም አንጥፋችሁ ትተኛላችሁ? ታዲያ እናንተ ጾም የምትሉት ይህን ነውን? እኔስ በዚህ ዐይነቱ ጾም ደስ የሚለኝ ይመስላችኋልን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እኔ የመረጥሁት ጾም እንዲህ ዐይነቱን ነውን? ሰውስ ራሱን የሚያዋርደው በእንዲህ ያለው ቀን ብቻ ነውን? እንደ ደንገል ራስን ዝቅ ማድረግ ነውን? ወይስ ማቅ ለብሶ በዐመድ ላይ መንከባለል ነውን? ታዲያ ጾም ብለህ የምትጠራው ይህን ነውን? እግዚአብሔርስ የሚቀበለው እንዲህ ያለውን ቀን ነውን?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነው? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነው? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ እንዲያደርግ፥ ማቅንና አመድንም በበታቹ እንዲያነጥፍ ነው? በውኑ ይህን ጾም፥ በጌታ ዘንድ የተወደደ ቀን ብለህ ትጠራዋለህ?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እኔ ይህን ጾም የመ​ረ​ጥሁ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ እን​ደ​ዚ​ችም ባለች ቀን ሰው ራሱን ቢያ​ሳ​ዝን፥ አን​ገ​ቱ​ንም እንደ ቀለ​በት ቢያ​ቀ​ጥን፥ ማቅ ለብሶ በአ​መድ ላይ ቢተ​ኛም፥ ይህ ጾም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​መ​ረጠ አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እኔ የመረጥሁት ጾም ይህ ነውን? ሰውስ ነፍሱን የሚያዋርደው እንደዚህ ባለ ቀን ነውን? በውኑ ራሱን እንደ እንግጫ ዝቅ ያደርግ ዘንድ ማቅንና አመድንም በበታቹ ያነጥፍ ዘንድ ነውን? በውኑ ይህን ጾም፥ በእግዚአብሔርም ዘንድ የተወደደ ቀን ትለዋለሁ?

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 58:5
22 Referencias Cruzadas  

ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ በሐዘን ልብሱን ቀደደ፤ በግንቡ ላይ በመሆኑ በአቅራቢያው የነበረው ሕዝብ ንጉሡ ከልብሱ በውስጥ በኩል ማቅ ለብሶ እንደ ነበር አዩ።


ኢዮሣፍጥ እጅግ ስለ ፈራ ፈቃዱን እንዲገልጥለት ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ ከዚህ በኋላ በመላው አገሪቱ ሕዝቡ ሁሉ እንዲጾም ትእዛዝ አስተላለፈ፤


ቀጥሎም ዕዝራ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ከነበረው ስፍራ በመነሣት የኤልያሺብ ልጅ ዮሐናን ወደሚኖርባቸው ክፍሎች ገባ፤ ምርኮኞቹ እምነት በማጓደል ስለ ፈጸሙትም በደል ሁሉ እያዘነ ሌሊቱን በዚያው አነጋ፤ እህልም ሆነ ውሃ አልቀመሰም።


እግዚአብሔር ጒዞአችንን እንዲያቃናልን፥ እኛንና ልጆቻችንን፥ እንዲሁም ንብረታችንን ሁሉ እንዲጠብቅልን በእርሱ ፊት ራሳችንን ዝቅ አድርገን እንለምነው ዘንድ በዚያው በአሀዋ ወንዝ አጠገብ ጾም ዐወጅኩ።


“ሄደህ በሱሳ የሚገኙትን አይሁድ በአንድነት ሰብስብ፤ ጾም ዐውጃችሁም ለእኔ ጸልዩ፤ እስከ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ምንም ዐይነት ምግብ አትብሉ፤ ምንም ዐይነት መጠጥ አትጠጡ፤ እኔና ደንገጡሮቼም በዚሁ ዐይነት እንቈያለን፤ ከዚህም በኋላ በሕግ የተከለከለ ቢሆንም ደፍሬ ወደ ንጉሡ ዘንድ እገባለሁ፤ ይህን በማድረጌ ብሞትም ልሙት።”


የንጉሡ ዐዋጅ በተላለፈባቸው አገሮች ሁሉ በአይሁድ መካከል ከፍተኛ የለቅሶ ጩኸት ተሰማ፤ እነርሱም መጾምና ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ማልቀስ ጀመሩ፤ አብዛኞቹም ማቅ ለብሰውና በራሳቸው ላይ ዐመድ ነስንሰው ተቀመጡ።


ከዚህም የተነሣ ኢዮብ በዐመድ ክምር ላይ ተቀምጦ ቊስሉን በገል ያክ ጀመር።


እግዚአብሔር ሆይ! እኔ ግን ወደ አንተ እጸልያለሁ፤ አንተ በመረጥከው ጊዜ ጸሎቴን መልሰህ፥ በዘለዓለማዊው ፍቅርህ ማዳንህን አረጋግጥልኝ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በመረጥኩት ሰዓት ለጸሎትህ መልስ እሰጥሃለሁ፤ በመዳንም ቀን እረዳሃለሁ፤ ምድሪቱን መልሰህ እንድታቋቋምና ውድማ የሆነውን መሬት እንድታከፋፍል ቃል ኪዳን አድርጌ ለሕዝቡ ሰጥቼሃለሁ።


ሕዝቡም “እነሆ እኛ እንጾማለን፤ አንተ ግን አትመለከተንም፤ የማትመለከተንስ ከሆነ ሰውነታችንን ለምን እናዋርዳለን?” ይላሉ። እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “እነሆ እናንተ በምትጾሙበት ጊዜ የልባችሁን ፈቃድ ትፈጽማላችሁ፤ ሠራተኞቻችሁንም ሁሉ ትጨቊናላችሁ፤


የእግዚአብሔርን የምሕረት ዓመትና የአምላካችንን የበቀል ቀን እንዳውጅ፥ የሚያለቅሱትን ሁሉ እንዳጽናና፥


“ከዚህ የሚከተሉትን መመሪያዎች በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ቋሚ ሥርዓት አድርጋችሁ ትጠብቁአቸዋላችሁ፦ ሰባተኛው ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን እስራኤላውያንና በእነርሱ መካከል የሚኖሩ መጻተኞች ራሳቸውን ማዋረድ አለባቸው፤ በዚያን ቀን ምንም ሥራ አይሥሩበት።


ያም ዕለት እንደ ሰንበት የዕረፍት ቀን ይሁንላችሁ፤ በዚያን ቀን ራሳችሁን አዋርዱ ይህም የዘለዓለም ሥርዓት ነው።


ለምድሪቱ ሕዝብ ሁሉና ለካህናቱ እንዲህ በላቸው፦ “ባለፉት ሰባ ዓመቶች በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር የጾማችሁትና ያዘናችሁት እኔን ለማክበር ነበርን?


ኢየሱስም ቀጥሎ እንዲህ አለ፦ “በምትጾሙበት ጊዜ፥ መጾማቸውን ሰዎች እንዲያውቁላቸው፥ ፊታቸውን እንደሚለውጡት እንደ ግብዞች፥ ፊታችሁን አታጠውልጉ፤ በእውነት እላችኋለሁ፥ እነርሱ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።


እንዲሁም ጌታ ሕዝቡን የሚያድንበትን የጸጋ ዓመት እንዳስታውቅ ልኮኛል።”


መልካሙንና ደስ የሚያሰኘውን ፍጹም የሆነውንም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ እንድትችሉ አእምሮአችሁን በማደስ ሕይወታችሁ ይለወጥ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉት።


ወደ ጌታ ኢየሱስ የምትቀርቡትም እንደ ሕያዋን ድንጋዮች መንፈሳዊ ቤት ሆናችሁ ለመታነጽ ነው፤ በዚህ ዐይነት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ቅዱሳን ካህናት ትሆናላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos