ኢሳይያስ 5:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 እነሆ የሠራዊት አምላክ እንዲህ ብሎ በመሐላ ሲያረጋግጥ ሰምቼአለሁ፦ “የተዋቡ ታላላቅ ቤቶች ሁሉ ፈርሰው ወና ይሆናሉ፤ የሚኖርባቸው ሰውም አይገኝም። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ጆሮዬ እየሰማ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “ታላላቅ ቤቶች ወና ይቀራሉ፣ የሚያማምሩም ቤቶች ኗሪ ያጣሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ጆሮዬ እየሰማ እንዲህ ሲል ተናገረ፤ “ታላላቅ ቤቶች ወና ይቀራሉ፤ የሚያማምሩም ቤቶች ነዋሪ ያጣሉ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ይህ በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ጆሮ ተሰምቶአልና፦ ቤቶች ቢሠሩ ባድማ ይሆናሉ፤ ታላላቅና የሚያምሩ ቤቶችም የሚቀመጥባቸው አይኖርም። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በጆሮዬ እንዲህ አለ፦ በእውነት ብዙ ታላቅና መልካም ቤት ባድማ ይሆናል፥ የሚቀመጥበትም አይገኝም። Ver Capítulo |