Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 45:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “እኔ በፊትህ እሄዳለሁ፤ ተራራዎችን ዝቅ አድርጌ እደለድላለሁ፤ በነሐስ የተሠሩ በሮችንና የብረት መወርወሪያዎችን እሰብራለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ‘በፊትህ እሄዳለሁ፤ ተራሮችን እደለድላለሁ፤ የናስ በሮችን እሰብራለሁ፤ የብረት መወርወሪያዎችንም እቈርጣለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በፊትህ እሄዳለሁ ተራሮችንም እደለድላለሁ፥ የናሱንም ደጆች እሰብራለሁ የብረቱንም መወርወሪያዎች እቈርጣለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “በፊ​ትህ እሄ​ዳ​ለሁ፤ ተራ​ሮ​ች​ንም ዝቅ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የና​ሱ​ንም ደጆች እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ የብ​ረ​ቱ​ንም መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎች እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በፊትህ እሄዳለሁ ተራሮችንም አደርጋለሁ፥ የናሱንም ደጆች እሰብራለሁ የብረቱንም መወርወሪያዎች እቈርጣለሁ፥

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 45:2
17 Referencias Cruzadas  

ከናስ የተሠሩትን በሮች ሰባበረ፤ የብረት መወርወሪያዎችንም ቈራረጠ።


ምንም ነገር በማይበቅልበት ተራራ ጫፍ ሆናችሁ ምልክት ስጡ፤ ወደ ትዕቢተኞቹ የባቢሎን ገዢዎች ወደሚያስገባው በር እንዲገቡ ትእዛዝ ስጡ።


በመግቢያው በር ሆናችሁ ወዮ በሉ! በከተማው ውስጥ ሆናችሁ ኡኡ! በሉ፤ ከወታደሮቹ አንዱ እንኳ ወደ ኋላ የማይል ኀይለኛ ጠላት ከሰሜን ስለ መጣ ፍልስጥኤማውያን ሁሉ በፍርሃት ይርበድበዱ!


ከተማይቱ የፍርስራሽ ክምር ሆናለች፤ በሮችዋም ተሰባብረው ወድቀዋል።


ጐድጓዳውና ሸለቆው ይሙላ፤ ተራራውና ኰረብታው ሁሉ ዝቅ ብሎ ይደልደል፤ ኮረብታውና ወጣ ገባ የሆነው ምድር ሁሉ ይስተካከል።


“ዕውሮችን ሄደውበት በማያውቁት መንገድ እመራቸዋለሁ፤ ቀድሞ ባላወቁትም መንገድ እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸው የተጋረደውንም ጨለማ ወደ ብርሃንነት እለውጣለሁ፤ ወጣገባ የሆነውንም ስፍራ አስተካክላለሁ፤ እነዚህ ነገሮች ሁሉ እኔ የምፈጽማቸው ናቸው፤ አልተዋቸውምም።


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “ቂሮስን ለጽድቅ ሥራ አነሣሥቼዋለሁ፤ መንገዱንም አቀናለታለሁ፤ ከተማዬን ኢየሩሳሌምን እንደገና ይሠራታል፤ በስደት ላይ ያሉ ሕዝቤንም ነጻ ያወጣል፤ ይህንንም የሚያደርገው ማንም ገንዘብ እንዲከፍለው ወይም ውለታውን እንዲመልስለት አይደለም።” የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሮአል።


እኔ ራሴ ተናግሬአለሁ፤ ጠርቼዋለሁም፤ እኔ አመጣዋለሁ፤ የእርሱም ተልእኮ የተሳካ ይሆናል።


“ሂድ! ለሐናንያ እንዲህ ብለህ ንገረው፦ ‘እነሆ አንተ የእንጨቱን ቀንበር ለመስበር ችለሃል፤ እኔ ግን በእርሱ ፈንታ የብረት ቀንበር እተካለሁ፤


የባቢሎን ወታደሮች ጦርነቱን አቁመው በምሽጋቸው ተቀመጡ፤ የጀግንነትን ወኔ አጥተው እንደ ሴቶች ሆኑ፤ የከተማይቱ የቅጽር በሮች መወርወሪያዎች ተሰባብረዋል፤ ቤቶችም በእሳት ተቃጥለዋል።


ሰፊው የባቢሎን ቅጽር ወድቆ ከመሬት ይደባለቃል፤ ከፍ ብለው የተሠሩ የቅጽር በሮችዋ በእሳት ይጋያሉ። የሕዝብዋ ድካም ከንቱ ይሆናል፤ ሕዝቦች የደከሙበት ነገር ሁሉ በእሳት ይወድማል። እኔ የሠራዊት አምላክ ይህን ተናግሬአለሁ።”


ፋርስ ‘መንግሥትህ ተከፍሎ ለሜዶናውያንና ለፋርስ ሰዎች ተሰጠ’ ማለት ነው።”


ያም በግ በቀንዶቹ ለመጐሸም ወደ ምዕራብ፥ ወደ ሰሜን፥ ወደ ደቡብ ሲቃጣ አየሁ፤ በፊቱ ቀርቦ የሚቋቋመው ወይም ከኀይሉ ማምለጥ የሚችል አውሬ አልነበረም፤ የፈለገውን ሁሉ ያደርግ ነበር፤ ይበልጥም እየበረታ ሄደ።


ወታደሮችሽ ሁሉ እንደ ሴት ፈሪዎች ሆነዋል፤ የጠረፍሽ በሮች ለጠላቶችሽ ክፍት ሆነዋል፤ መወርወሪያዎቹም እሳት በልቶአቸዋል።


ጐድጓዳው ቦታ ሁሉ ይደልደል! ተራራና ኰረብታውም ሁሉ ዝቅ ይበል! ጠማማው መንገድ ይቅና! ሻካራውም መንገድ ይስተካከል!


በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መቶ ኻያ በሚያኽሉ አማኞች መካከል ቆመና እንዲህ አለ፦


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos