Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 38:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ሕዝቅያስም ከሕመሙ እንደ ተፈወሰ የሚከተለውን የምስጋና መዝሙር ጻፈ፦

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ከሕመሙ ከተፈወሰ በኋላ የጻፈው ጽሕፈት፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ታሞ ከበሽታው በተፈወሰ ጊዜ የጻፈው ጽሑፍ ይህ ነው፦

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የይ​ሁዳ ንጉሥ ሕዝ​ቅ​ያስ ታምሞ ከደ​ዌው በተ​ፈ​ወሰ ጊዜ የጸ​ለ​የው ጸሎት ይህ ነው፦

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ታምሞ ከደዌው በተፈወሰ ጊዜ የጻፈው ጽሕፈት ይህ ነው፦

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 38:9
16 Referencias Cruzadas  

ንጉሡና የሕዝቡ መሪዎች ሁሉ በዳዊትና በነቢዩ አሳፍ የተደረሱትን የምስጋና መዝሙሮች ለእግዚአብሔር ክብር እንዲዘምሩ ሌዋውያንን አዘዙ፤ ስለዚህ ሁሉም ተንበርክከው በመስገድ ላይ ሳሉ በታላቅ ደስታ ይዘምሩ ነበር።


እግዚአብሔር ቢያቈስልህም መልሶ ይጠግንሃል፤ በአንድ እጁ ቢጐዳህ በሌላ እጁ ይፈውስሃል።


እግዚአብሔር ሆይ! ኀይል የምትሰጠኝ አንተ ስለ ሆንክ፥ እወድሃለሁ።


እኔ ገና በመካከለኛ ዕድሜዬ ሳለሁ የመኖር ዕድል ተነፍጎኝ ወደ ሙታን ዓለም የምወርድ መስሎኝ ነበር።


ንጉሥ አካዝ ባሠራው የመወጣጫ ደረጃ ላይ የሚያርፈውን ጥላ እግዚአብሔር እንደገና ዐሥር ደረጃዎችን አልፎ ወደ ኋላ እንዲመለስ ያደርገዋል።” ጥላውም ዐሥር ደረጃዎችን አልፎ ወደ ኋላ ተመለሰ።


“አምላክ እኔ ብቻ መሆኔን ዕወቁ፤ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ የምገድልም፥ ሕይወትንም የምሰጥ እኔ ነኝ፤ አቈስላለሁ፤ እፈውሳለሁም ከእጄ ማንም ሊያድን አይችልም


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos