Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዕብራውያን 13:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከእነርሱ ጋር አብራችሁ እንደ ታሰራችሁ ያኽል ሆናችሁ እስረኞችን አስታውሱ፤ እናንተም እንደ እነርሱ መከራ የምትቀበሉ ያኽል ሆናችሁ መከራ የሚቀበሉትን አስቡ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በእስር ላይ ያሉትን ከእነርሱ ጋራ እንደ ታሰራችሁ ሆናችሁ አስቧቸው፤ እንዲሁም በሰው እጅ የሚንገላቱትን ራሳችሁ መከራ እንደምትቀበሉ አድርጋችሁ አስቧቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እስረኞችን አብራችኋቸው እንደታሰረ ሆናችሁ አስቡ፤ እናንተም በሥጋ እንዳለ እያሰባችሁ የተጨነቁትንም እንደራሳችሁ አስቡ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከእ​ነ​ርሱ ጋር አብ​ራ​ች​ኋ​ቸው እንደ ታሰ​ራ​ችሁ ሆና​ችሁ እስ​ረ​ኞ​ችን ዐስቡ፤ መከራ የጸ​ና​ባ​ቸ​ው​ንም በሥ​ጋ​ችሁ ከእ​ነሱ ጋር እን​ዳ​ላ​ችሁ ሆና​ችሁ ዐስቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ከእነርሱ ጋር እንደ ታሰረ ሆናችሁ እስሮችን አስቡ፥ የተጨነቁትንም ራሳችሁ ደግሞ በሥጋ እንዳለ ሆናችሁ አስቡ።

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 13:3
19 Referencias Cruzadas  

ታርዤ ነበር፥ አልብሳችሁኛል፤ ታምሜ ነበር፥ ጠይቃችሁኛል፤ ታስሬ ነበር መጥታችሁ ጐብኝታችሁኛል።’


እናንተ የተሻለና ነዋሪ ሀብት በሰማይ እንዳላችሁ በማወቃችሁ ለእስረኞች ራራችሁላቸው፤ ንብረታችሁም ሲወሰድባችሁ ታግሣችሁ ሁኔታውን በደስታ ተቀበላችሁ።


ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱም ጋር አልቅሱ።


አንዱ የአካል ክፍል ሲሠቃይ ሌሎችም የአካል ክፍሎች በሙሉ አብረው ይሠቃያሉ፤ አንዱ የሰውነት ክፍል ሲከበር ሌሎቹም የሰውነት ክፍሎች አብረው ከእርሱ ጋር ይደሰታሉ።


ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ የጻፍኩት እኔ ጳውሎስ ነኝ፤ በሰንሰለት ታስሬ እንዳለሁ አስታውሱ። የእግዚአብሔር ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።


በቀረውስ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ በመስማማት ኑሩ፤ የሌላውን ሰው ችግር እንደ ራሳችሁ አድርጋችሁ ቊጠሩ፤ በወንድማማችነት ፍቅር ተዋደዱ፤ ደጎችና ትሑቶች ሁኑ።


እንግዳ ሆኜ መጥቼ ነበር፥ አልተቀበላችሁኝም፤ በቤታችሁ ታርዤ ነበር፥ አላለበሳችሁኝም፤ ታምሜና ታስሬ ነበር፥ አልጠየቃችሁኝም፤’


ጳውሎስን ይጠብቅ የነበረውንም መቶ አለቃ “እምብዛም ነጻነት ሳትከለክለው በጥንቃቄ ጠብቀው፤ ወዳጆቹም የሚያስፈልገውን ሁሉ ይዘውለት ሲመጡ አትከልክልበት” አለው።


እንግዲህ ጌታን በማገልገሌ እስረኛ የሆንኩ እኔ፥ ለተጠራችሁበት ጥሪ ተገቢ የሆነ ሕይወት ትኖሩ ዘንድ እለምናችኋለሁ።


በማግስቱ ወደ ሲዶና ደረስን፤ ዩልዮስ ለጳውሎስ ደግ ስለ ነበረ ወደ ወዳጆቹ ሄዶ የሚያስፈልገውን ርዳታ እንዲያደርጉለት ፈቀደለት።


የወይን ጠጅ አሳላፊው ግን ዮሴፍን አላስታወሰውም፤ ስለ ዮሴፍ የሆነውን ሁሉ ረሳ።


በድንጋይ ተወገሩ፤ በመጋዝ ተሰነጠቁ፤ በሰይፍ ተገደሉ፤ የበግና የፍየል ቆዳ ለብሰው ተንከራተቱ፤ ድኾችና ስደተኞች ሆነው ተንገላቱ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios