Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 9:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ነገር ግን በደሙ ውስጥ ሕይወት ስላለ ደም ያለበትን ሥጋ አትብሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 “ነገር ግን ሕይወቱ፣ ማለት ደሙ ገና በውስጡ ያለበትን ሥጋ አትብሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ነገር ግን ደም ያለችበትን ሥጋ አትብሉ፥ ምክንያቱም በደም ውስጥ ሕይወት አለ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ነገር ግን ደመ ነፍስ ያለ​በ​ትን ሥጋ አት​ብሉ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ነገር ግን ነፍሱ ደሙ ያለችበትን ሥጋ አትብሉ፥

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 9:4
15 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን የሕይወት መኖሪያ በደም ውስጥ ስለ ሆነ ደም ያለበትን ሥጋ ከመብላት ብቻ ተጠንቀቅ፤ ስለዚህ ሕይወትን ከሥጋ ጋር አትብላ።


ደማቸውን እንደ ምግብ አድርጋችሁ አትመገቡት፤ ነገር ግን ደሙን እንደ ውሃ በምድር ላይ አፍስሱት።


ነገር ግን ደማቸውን አትብላ፤ ደሙን እንደ ውሃ በመሬት ላይ አፍስሰው፤


ይልቅስ ‘ለጣዖት በመሠዋቱ ምክንያት የረከሰ ምግብን አትብሉ፤ ከዝሙት ራቁ፤ ሳይታረድና ደሙም ሳይፈስ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋን አትብሉ፤ ደምንም አትብሉ’ ብለን እንጻፍላቸው።


እንዲሁም እስራኤላውያን የትም ቦታ ቢኖሩ በሚኖሩበት ስፍራ ሁሉ የወፍም ሆነ የእንስሳ ደም አይብሉ፤


ለጣዖት በመሠዋቱ ምክንያት የረከሰ ምግብ አትብሉ፤ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋን አትብሉ፤ ደምም አትብሉ፤ ከዝሙት ራቁ፤ ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ ብትጠበቁ መልካም ታደርጋላችሁ፤ ደኅና ሁኑ።”


ከእስራኤላውያን ወገን ስብ የሆነውን ሥጋ ወይም የእንስሶችን ደም የሚመገብ አይኑር፤ ይህም እስራኤላውያን በሚኖሩበት ዘመንና ቦታ ሁሉ ለዘለዓለሙ ተጠብቆ የሚኖር ቋሚ ሥርዓት ይሁን።


ዳሩ ግን እግዚአብሔር የፈጠረው ነገር ሁሉ መልካም ነው፤ በምስጋና ከተቀበሉት ምንም የሚጣል ነገር የለም።


“ደም ያለበትን ሥጋ አትብሉ፤ የአስማትን ነገር አትከተሉ፤


ስለዚህ በአንድነት ከተሰበሰብን በኋላ መልእክተኞችን መርጠን ከተወደዱት ወንድሞቻችን ከበርናባስና ከጳውሎስ ጋር ወደ እናንተ ልንልካቸው ተስማማን።


“ሞቶ የተገኘውን እንስሳ አትብላ፤ በመካከልህ የሚኖሩ የውጪ አገር ሰዎች እንዲመገቡት ፍቀድላቸው፤ ወይም ለውጪ አገር ሰዎች በዋጋ ልትሸጥላቸው ትችላለህ። አንተ ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተለየህ ሕዝብ ነህ። “የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።


ስለዚህም ከጠላት ባገኙት ምርኮ ላይ እየተረባረቡ በጎችን፥ የቀንድ ከብቶችንና ጥጆችን ባገኙበት ቦታ እያረዱ ሥጋውን ከነደሙ መብላት ጀመሩ፤


“እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የምለውን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ ‘ሥጋ ከነደሙ ትበላላችሁ፤ ጣዖት ታመልካላችሁ፤ ግድያ ትፈጽማላችሁ፤ ታዲያ፥ ይህን ሁሉ እያደረጋችሁ እንዴት ምድሪቱ የእኛ ርስት ናት ትላላችሁ?


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios