Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 42:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 ሮቤል አባቱን እንዲህ አለው፤ “ብንያምን ወደ አንተ መልሼ ባላመጣው ሁለቱን ወንዶች ልጆቼን ወስደህ ግደላቸው፤ ስለዚህ በእኔ ኀላፊነት ላከው፤ እኔም መልሼ አመጣዋለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 በዚህ ጊዜ ሮቤል አባቱን፣ “መልሼ ባላመጣው፣ ሁለቱን ወንዶች ልጆቼን ግደላቸው፤ ኀላፊነቱን ለእኔ ተውልኝ፤ እኔው መልሼ አመጣዋለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 በዚህን ጊዜ ሮቤል አባቱን፥ “መልሼ ባላመጣው፥ ሁለቱን ወንዶች ልጆቼን ግደላቸው፤ ኀላፊነቱን ለእኔ ተውልኝ፤ እኔው መልሼ አመጣዋለሁ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 ሮቤ​ልም አባ​ቱን አለው፥ “ወደ አንተ መልሼ ያላ​መ​ጣ​ሁት እን​ደ​ሆነ ሁለ​ቱን ልጆ​ችን ግደል፤ ልጅ​ህን በእጄ ስጠኝ፤ እኔም ወደ አንተ እመ​ል​ሰ​ዋ​ለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 ሮቤልም አባቱን አለው፦ ወደ አንተ መልሼ ያላመጣሁት እንደ ሆነ ሁለቱን ልጆቼን ግደል እርሱን በእጄ ስጠኝ እኔም ወደ አንተ እመልሰዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 42:37
6 Referencias Cruzadas  

በሺህ የሚቈጠሩ አውራ በጎችን ወይም የዐሥር ሺህ ወንዞችን ውሃ የሚያኽል የወይራ ዘይት ባቀርብለት ይደሰት ይሆን? ስለ በደሌና ስለ ኃጢአቴ የበኲር ልጄን ልሠዋለትን?


የሮቤል ልጆች፦ ሔኖክ፥ ፋሉ፥ ሔጽሮንና ካርሚ ናቸው።


ልጁን በእኔ ዋስትና ስጠኝ፤ ስለ እርሱ እኔ ተጠያቂ እሆናለሁ፤ በደኅና ወደ አንተ መልሼ ባላመጣው በሕይወቴ ዘመን ተወቃሽ ልሁን።


በዚህ ጊዜ አባታቸው “ልጆቼን ሁሉ እንዳጣ ትፈልጋላችሁን? ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ለመውሰድ ትፈልጋላችሁ፤ በዚህ ሁሉ መከራ የምሠቃየው እኔ ነኝ!” አለ።


ያዕቆብም “ምንም ቢሆን ከእናንተ ጋር አይሄድም፤ ወንድሙ ሞቶአል፤ የቀረው እርሱ ብቻ ነው፤ በመንገድ አንድ ጒዳት ቢደርስበት በእርጅናዬ ዘመን በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር እንድወርድ ታደርጉኛላችሁ” አላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios