Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 42:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ያዕቆብ በግብጽ እህል መኖሩን በሰማ ጊዜ ልጆቹን “እርስ በርሳችሁ እየተያያችሁ የምትቀመጡት ለምንድን ነው?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ያዕቆብ በግብጽ እህል መኖሩን ሲሰማ፣ ልጆቹን እንዲህ አላቸው፤ “ለምን እርስ በርስ ትተያያላችሁ?

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ያዕቆብ በግብጽ እህል መኖሩን ሲሰማ፥ ልጆቹን እንዲህ አላቸው፤ “ለምን እርስ በርስ ትተያያላችሁ?

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ያዕ​ቆ​ብም በግ​ብፅ የሚ​ሸ​መት እህል እን​ዳለ ሰማ፤ ልጆ​ቹ​ንም፥ “ለምን ትተ​ክ​ዛ​ላ​ችሁ?” አላ​ቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ያዕቆብም በግብፅ እህል እንዳለ ስማ ያዕቆብም ልጆቹን፦ ለምን እርስ በርሳችሁ ትተያያላችሁ? አላቸው

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 42:1
13 Referencias Cruzadas  

ያዕቆብም በግብጽ እህል መኖሩን በሰማ ጊዜ ለመጀመሪያ ጊዜ አባቶቻችንን ወደዚያ ላከ።


እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፤ “ተነሥ! ስለምን በግንባርህ ወደቅኽ?


እንዲያውም እግዚአብሔር ጴጥሮስን ለአይሁድ የምሥራቹን ቃል እንዲያበሥር በተላከው ዐይነት እኔንም የምሥራቹን ቃል ለአሕዛብ እንዳበሥር እንዳደረገኝ ተገነዘቡ፤


“እስራኤል መታመሙን፥ ይሁዳም መቊሰሉን ባየ ጊዜ፥ እስራኤል ወደ አሦር ፊቱን መለሰ፤ ርዳታም ለማግኘት ወደ ታላቁ ንጉሥ መልእክተኛ ላከ፤ ነገር ግን እርሱ ሊያድናቸው ወይም ቊስላቸውን ሊፈውስ አልቻለም።


የእግዚአብሔር ሕዝብ እንዲህ ይላሉ፦ “ዝም ብለን መቀመጣችን ለምንድን ነው? አምላካችን እግዚአብሔር ሞት ፈርዶብናል፤ እርሱን ስለ በደልን የተመረዘ ውሃ እንድንጠጣ አድርጎናል። ኑ! ወደተመሸጉ ከተሞች ሮጠን እዚያ እንሙት፤


ይህንንም ሁሉ ለማስፈጸም ኀላፊነቱ የአንተ ስለ ሆነ ተነሥ፤ እኛም እንደግፍሃለን፤ አይዞህ በርታ።”


ኤልያስም ስለ ፈራ ሕይወቱን ለማትረፍ ከአገልጋዩ ጋር በይሁዳ ወደምትገኘው ወደ ቤርሳቤህ ከተማ ሄደ። አገልጋዩንም በዚያ ተወው፤


ሕዝቡም የነጐድጓዱንና የእምቢልታውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ እንዲሁም መብረቁ ሲብለጨለጭና ተራራው ሲጤስ ባዩ ጊዜ በፍርሃት በመንቀጥቀጥ ርቀው ቆሙ፤


የእስራኤላውያን ሠራተኞች አለቆች ቀድሞ የሚሠሩትን ያኽል ጡብ በየቀኑ መሥራት እንዳለባቸው በተረዱ ጊዜ በመከራ ላይ መውደቃቸውን ተገነዘቡ።


በግብጽ አገር እህል መኖሩን ሰምቼአለሁ፤ በራብ እንዳንሞት ወደዚያ ሂዱና እህል ሸምቱልን” አላቸው።


በዓለም ላይ ራብ ጸንቶ ስለ ነበር የልዩ ልዩ አገር ሕዝቦች ከዮሴፍ እህል ለመግዛት ወደ ግብጽ አገር መጡ።


ዮሴፍ አስቀድሞ እንደ ተናገረው፥ ሰባቱ የራብ ዓመቶች መግባት ጀመሩ፤ በሌሎች አገሮች ሁሉ ራብ ሆነ፤ ይሁን እንጂ በመላው የግብጽ ምድር በቂ ምግብ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios