Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 41:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 የቀጨጩትም ዛላዎች የሚያምሩትን ዛላዎች ዋጡአቸው፤ ያየኋቸውንም ሕልሞች ለአስማተኞች ነገርኩ፤ ነገር ግን ሕልሞቹን ማንም ሊተረጒምልኝ አልቻለም።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 የቀጨጩት የእሸት ዛላዎችም ሰባቱን ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዋጧቸው፤ ይህንኑም ለአስማተኞች ነገርሁ፤ ነገር ግን ማንም ሊፈታው አልቻለም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 የቀጨጩት የእሸት ዛላዎችም ሰባቱን ያማሩ የእሸት ዛላዎች ዋጧቸው፤ ይህንኑም ለአስማተኞች ነገርሁ፤ ነገር ግን ማንም ሊፈታው አልቻለም።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 እነ​ዚያ የሰ​ለ​ቱ​ትና በነ​ፋስ የተ​መ​ቱት እሸ​ቶች እነ​ዚ​ያን ያማ​ሩ​ት​ንና የጐ​መ​ሩ​ትን ሰባ​ቱን እሸ​ቶች ዋጡ​አ​ቸው። ለሕ​ልም ተር​ጓ​ሚ​ዎ​ችም ሕል​ሜን ነገ​ርሁ፤ የተ​ረ​ጐ​መ​ል​ኝም የለም።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 የሰለቱት እሸቶች ያማሩትን ሰባቱን እሸቶች ዋጡአቸው። ለሕልም ተርጓሚዎችም ሕልሜን ነገርሁ የሚተረጕምልኝም አጣሁ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 41:24
5 Referencias Cruzadas  

ቀጥሎም የቀጨጩና በበረሓ ነፋስ ተመተው የሰለቱ ሰባት የእሸት ዛላዎች ታዩ።


ጠዋት ከመኝታው ሲነሣ መንፈሱ ታወከ፤ ስለዚህ በግብጽ ምድር ያሉትን አስማተኞችና ጥበበኞች ሁሉ አስጠርቶ ሕልሙን ነገራቸው፤ ነገር ግን የሕልሞቹን ትርጒም ለመግለጥ የቻለ አንድ እንኳ አልነበረም።


አስማተኞቹም “ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ነው!” ብለው ለንጉሡ ነገሩት፤ ንጉሡ ግን ልቡን አደነደነ፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረውም ሙሴንና አሮንን መስማት አልፈለገም።


“በመንተባተብ የሚቀባጥሩትን ሟርተኞችንና የሙታን መናፍስት ጠሪዎችን ጠይቁ” እያሉ የሚሰብኩአችሁ ወገኖች አሉ፤ ታዲያ፥ ስለ ሕያዋን ሙታንን ከመጠየቅ ይልቅ ሕዝቡ አምላኩን መጠየቅ አይገባውምን?


ጠንቋዮች፥ አስማተኞች፥ ኮከብ ቈጣሪዎችና መተተኞች ሁሉ ወደ እኔ በመጡ ጊዜ ሕልሜን ነገርኳቸው፤ እነርሱ ግን የሕልሜን ትርጒም ሊነግሩኝ አልቻሉም፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos