Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 28:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ወደ አባቴም ቤት በሰላም ብትመልሰኝ፥ አንተ አምላኬ ትሆናለህ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ወደ አባቴ ቤትም በደኅና ቢመልሰኝ፣ እግዚአብሔር አምላኬ ይሆናል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ወደ አባቴ ቤትም በጤና ብመለስ፥ እግዚአብሔር አምላኬ ይሆንልኛል፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ወደ አባ​ቴም ቤት በጤና ቢመ​ል​ሰኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላኬ ይሆ​ን​ል​ኛል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የምበላውንም እንጀራ የምለብሰውንም ልብስ ቢሰጠኝ ወደ አባቴ ቤትም በጤና ብመለስ እግዚአብሔር አምላኬ ይሆንልኛል፤

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 28:21
8 Referencias Cruzadas  

ድል አድርጌ ከዘመቻ ወደ ቤቴ በደኅና ስመለስ ከቤት ወጥቶ ሊቀበለኝ የሚመጣው ለአንተ ይሆናል፤ እርሱንም ለአንተ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጌ አቀርበዋለሁ።”


እግዚአብሔር አምላክህ መሆኑንና በሕጉም የምትመራ መሆንህን ዛሬ አንተ አረጋግጠሃል፤ ሥርዓቱን፥ ትእዛዞቹንና ሕጎቹን ለመጠበቅና ታዛዥ ለመሆን ቃል ገብተሃል፤


ከዚህ በኋላ የሳኦል የልጅ ልጅ መፊቦሼት ንጉሡን ለመቀበል ወረደ፤ ንጉሡ ከኢየሩሳሌም ከወጣበት ጊዜ አንሥቶ አሁን በድል አድራጊነት እስከ ተመለሰበት ጊዜ ድረስ መፊቦሼት እግሩን አልታጠበም፤ ጢሙን አልተላጨም፤ ልብሱንም አላጠበም።


እኔ አገልጋይህ በሶርያ በምትገኘው በገሹር በኖርኩበት ጊዜ ‘ወደ ኢየሩሳሌም ብትመልሰኝ መሥዋዕት አቀርብልሃለሁ’ ብዬ ለእግዚአብሔር ስእለት ተስዬ ነበር።”


እግዚአብሔር በመዝሙር የማመሰግነው መከላከያ ኀይሌ ነው፤ ከጠላት እጅ ያዳነኝ ታዳጊዬም እርሱ ነው፤ እርሱ አምላኬ ስለ ሆነ አመሰግነዋለሁ፤ የአባቴም አምላክ ስለ ሆነ፥ ስለ ገናናነቱ እዘምራለሁ።


ስለዚህም ንዕማን እንዲህ አለ፦ “ስጦታዬን የማትቀበለኝ ከሆነ ከአሁን ጀምሮ ለእግዚአብሔር ብቻ እንጂ ለሌሎች ባዕዳን አማልክት የሚቃጠልም ሆነ ወይም ሌላ ዐይነት መሥዋዕት ስለማላቀርብ የሁለት በቅሎ ጭነት ዐፈር ይዤ እንድሄድ ፍቀድልኝ፤


መፊቦሼትም “ንጉሥ ሆይ! ሁሉንም ሀብት ጺባ ይውሰደው፤ ለእኔ አንተ በሰላም ወደ ቤትህ መመለስህ ብቻ ይበቃኛል” አለ።


ያዕቤጽም “አምላኬ ሆይ፥ ባርከኝ፤ ሰፊ ምድርንም ስጠኝ፤ እጅህ ከእኔ ጋር ይሁን፤ ሥቃይ ሊያስከትልብኝ ከሚችል ከማንኛውም ክፉ ነገር ጠብቀኝ” በማለት ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios