Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 22:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 በቱኤል ርብቃን ወለደ፤ ሚልካ እነዚህን ስምንት ልጆች ለአብርሃም ወንድም ለናኮር ወለደችለት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ባቱኤልም ርብቃን ወለደ። ሚልካ ለአብርሃም ወንድም ለናኮር የወለደችለት እነዚህ ስምንት ወንዶች ልጆች ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 በቱኤል ርብቃን ወለደ፤ ሚልካ እነዚህን ስምንት ልጆች ለአብርሃም ወንድም ለናኮር ወለደችለት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ባቱ​ኤ​ልም ርብ​ቃን ወለደ፤ ሚልካ ለአ​ብ​ር​ሃም ወን​ድም ለና​ኮር የወ​ለ​ደ​ች​ለት ስም​ንቱ ልጆች እነ​ዚህ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ባቱኤልም ርብቃን ወለድ፤ እነዚህን ስምንቱን ሚልካ ለአብርሃም ወንድም ለናኮር ወለደች።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 22:23
13 Referencias Cruzadas  

አብራም ሣራይን አገባ፤ ናኮር ደግሞ ሚልካን አገባ፤ እርስዋም ዪስካንን የወለደ የሃራን ልጅ ናት።


ኬሠድ፥ ሐዞ፥ ፊልዳሽ፥ ይድላፍና በቱኤል ናቸው።


ረኡማ የተባለችው የናኮር ቊባት ደግሞ ጤባሕን፥ ገሐምን፥ ተሐሽንና፥ ማዕካን ወለደችለት።


ገና ጸሎቱን ሳይጨርስ ርብቃ እንስራ ተሸክማ መጣች፤ የዚህችም ልጅ አባት በቱኤል ይባል ነበር፤ እርሱም የአብርሃም ወንድም ናኮር ከሚስቱ ከሚልካ የወለደው ነው።


እርስዋም “የባቱኤል ልጅ ነኝ፤ ባቱኤልም ሚልካ ለናኮር የወለደችለት ነው፤


እኔም ‘የማን ልጅ ነሽ?’ ብዬ ጠየቅኋት። እርስዋም ‘የባቱኤል ልጅ ነኝ፤ የባቱኤል አባት ናኮር እናቱም ሚልካ ይባላሉ’ አለችኝ። ከዚህ በኋላ ጒትቻ በጆሮዋ ላይ፥ አንባሮቹንም በእጆችዋ ላይ አደረግሁላት፤


ርብቃ ይህችውልህ፤ እነሆ፥ ይዘሃት ሂድ፤ እግዚአብሔር ራሱ እንደ ተናገረው ለጌታህ ልጅ ሚስት ትሁን” አሉት።


“አንቺ እኅታችን የብዙ ሺህ ሕዝብ እናት ሁኚ፤ ዘሮችሽም የጠላቶቻቸውን ከተሞች ይውረሱ!” ብለው ርብቃን መረቁአት።


ከዚህ በኋላ ይስሐቅ እናቱ ሣራ ትኖርበት ወደነበረው ድንኳን ርብቃን ይዞአት ገባ፤ ሚስትም ሆነችው፤ ይስሐቅ ርብቃን ወደዳት፤ በእናቱ ሞት ምክንያት ከደረሰበትም ሐዘን በዚህ ሁኔታ ተጽናና።


ይስሐቅ የባቱኤልን ልጅ ርብቃን ሲያገባ አርባ ዓመት ሆኖት ነበር፤ የርብቃ አባት ባቱኤልና ወንድምዋ ላባ በመስጴጦምያ የሚኖሩ ሶርያውያን ነበሩ፤


ይልቅስ ተነሥተህ በመስጴጦምያ ወዳለው ወደ እናትህ አባት ወደ ባቱኤል ቤት ሂድ፤ እዚያም ከአጐትህ ከላባ ሴቶች ልጆች አንዷን አግባ፤


በዚህ ሁኔታ ይስሐቅ ያዕቆብን አሰናበተው፤ ያዕቆብም በመስጴጦምያ ወደሚኖረው ወደ ላባ ሄደ፤ ላባ የያዕቆብና የዔሳው እናት የርብቃ ወንድም ነበረ፤ አባቱም ሶርያዊው ባቱኤል ነበር።


ይህም ብቻ ሳይሆን ርብቃ የነገድ አባታችን ከሆነው ከይስሐቅ መንታ ልጆችን በፀነሰች ጊዜ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos