ዘፍጥረት 18:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 አብርሃም እርጎ፥ ወተትና ሥጋ ይዞ ሄደና ምግቡን ለእንግዶቹ አቀረበላቸው፤ እነርሱ ምግቡን በሚበሉበት ጊዜ አብርሃም ከዛፉ ሥር አጠገባቸው ቆሞ ያስተናግዳቸው ነበር። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 አብርሃምም ርጎ፣ ወተትና የተዘጋጀውን የጥጃ ሥጋ አቀረበላቸው፤ ሲበሉም ዛፉ ሥር አጠገባቸው ቆሞ ነበር። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 እርጎና ወተት፥ ያዘጋጀውንም ጥጃ አመጣ፥ በፊታቸውም አቀረበው፥ እርሱም ከዛፉ በታች በፊታቸው ቆሞ ነበር፥ እነርሱም በሉ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 እርጎና መዓር፥ ያን ያዘጋጀውንም ጥጃ አመጣ፤ በፊታቸውም አቀረበው፤ እርሱም ከዛፉ በታች በፊታቸው ቆሞ ያሳልፍላቸው ነበር፤ እነርሱም በሉ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 እርጎን ወተትም ያዘጋጀውንም ጥጃ አመጣ በፊታቸውም አቀረበው፤ እርሱም ከዛፉ በታች በፊታቸው ቆሞ ነበር እነርሱም በሉ። Ver Capítulo |