Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 17:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 አብርሃምም እግዚአብሔርን፦ “እስማኤልን በፊትህ ብታኖረው ምንኛ መልካም ነበር” አለው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 አብርሃም እግዚአብሔርን፣ “እስማኤልን ብቻ ባርከህ ባኖርህልኝ” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 አብርሃምም እግዚአብሔርን፥ “እስማኤል በፊትህ ቢኖር በወደድሁ ነበር” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 አብ​ር​ሃ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አለው፥ “ይህ ይስ​ማ​ኤል ብቻ በፊ​ትህ ይኖ​ር​ልኝ ዘንድ አቤቱ፥ እማ​ል​ድ​ሃ​ለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 አብርሃምም እግዚአብሔርን፥ እስማኤል በፊትህ ቢኖር በወደድሁ ነበር አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 17:18
10 Referencias Cruzadas  

የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ፥ ጌታ አምላካችን ወደ እርሱ ለሚጠራቸው፥ በሩቅ ላሉትም ሁሉ ነው።”


ስለ ቅንነቴ እኔን ትረዳኛለህ፤ በፊትህም ለዘለዓለም ታኖረኛለህ።


“መልካሙን ነገር ማን ያሳየናል?” የሚሉ ብዙዎች ናቸው፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ! የፊትህ ብርሃን በእኛ ላይ ይብራ!


አንድ ዓላማ እንዲኖራቸው አደርጋለሁ፤ ይኸውም ለእነርሱና ለልጆቻቸው ሁሉ መልካም ነገር እንዲሆንላቸው ዘወትር ያከብሩኝ ዘንድ ነው።


በደላችሁ በእናንተና በእግዚአብሔር መካከል ሆኖ ጋረደ፤ ኃጢአታችሁ ከእግዚአብሔር ስለ ለያችሁ ጸሎታችሁ አይሰማም።


እነሆ፥ ዛሬ ከምድር አባረርከኝ፤ ከፊትህም እሰወራለሁ፤ በምድርም ላይ ስደተኛና ተንከራታች እሆናለሁ፤ እንግዲህ ማንም ሰው ቢያገኘኝ ይገድለኛል።”


ምድርንም በምታርስበት ጊዜ ምንም ፍሬ አትሰጥህም፤ በምድር ላይም ስደተኛ ሆነህ ትንከራተታለህ።”


አብርሃም ግንባሩ መሬት እስኪነካ ድረስ ዝቅ ብሎ ሰገደ፤ ነገር ግን “ዕድሜው መቶ ዓመት የሆነው ሰው ልጅ መውለድ ይችላልን? ሣራስ በዘጠና ዓመትዋ ልጅ ልትወልድ ትችላለችን?” ብሎ በማሰብ ሳቀ፤


እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እንዲህስ አይሆንም፤ ነገር ግን ሚስትህ ሣራ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ይስሐቅ ትለዋለህ፤ ቃል ኪዳኔን ከእርሱና ከዘሩ ጋር ለዘለዓለም አጸናለሁ፤


አብርሃምም ስለ ልጁ ስለ እስማኤል በብርቱ ተጨነቀ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios