ዘፀአት 38:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 ለተቀደሰው ድንኳን መግቢያ ክፍል መጋረጃዎችን ከጥሩ በፍታ ሠራ፤ የመጋረጃዎቹም ርዝመት በደቡብ በኩል አርባ አራት ሜትር ነበር፤ Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 ቀጥሎም አደባባዩን ሠሩ፤ የደቡቡ ክፍል ርዝመት አንድ መቶ ክንድ ሲሆን፣ በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ የተሠሩ መጋረጃዎች ነበሩት፤ Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 አደባባዩንም ሠራ፤ በደቡብ በኩል የአደባባዩ መጋረጃዎች ርዝመቱ መቶ ክንድ የሆነ፥ ከጥሩ በፍታ የተፈተለ ነበር። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ለድንኳኑም በደቡብ በኩል በስተቀኝ አደባባይ አደረገ፤ የአደባባዩ መጋረጃም ከተፈተለ ጥሩ በፍታ የተሠራ ርዝመቱ መቶ ክንድ ነበረ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 አደባባዩንም አደረገ፤ በደቡብ ወገን ርዝመቱ መቶ ክንድ የሆነ፥ የተፈተለ የጥሩ በፍታ መጋረጆች ነበሩ። Ver Capítulo |